Fana: At a Speed of Life!

አቶ አገኘሁ ተሻገር የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው የመስቀል ደመራ በዓልን ሁሌም የምናከብረው የመከራ ዘመን አልፎ የዕረፍትና የሰላም ዘመን እንዲመጣ መስቀሉን ከተረሳበት ለማውጣት ለንግስት እሌኒ ፈጣሪ የሰጣትን ፀጋ እያሰብን ነው ብለዋል።

የመስቀሉ መገኘት ምሳሌው ብዙ ነው በተለይም የግፍ እና የመከራ ዘመን አልፎ የእረፍትና የሰላም ዘመን መምጣት አይቀሬነትን እንዲሁም እውነት ትዘገይ እንደሆን እንጂ ተደብቃ እንደማትቀር ያስተምረናል ነው ያሉት ።

ምንም እንኳን ፈተናና መከራችን ቢበዛም እውነት እና ፍትህ ከኛ ጋር ነችና በአሸናፊነት እንደምንሻገረው ከቶ አንጠራጠርም ብለዋል፡፡

የወቅቱ ፍልሚያም ሀገርን ለማጥፋት ባሴሩ ክፉዎች እና ሀገርን ለማዳን በተሰለፉ ወገኖች መካከል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ እኛ ያልገዛናት ሀገር ከምድረ ገፅ ትጥፋ በሚል ከእነ ግብረአበሮቻቸው ተማምለው በውጭ ሀይሎች የእጅ አዙር ድጋፍ ጭምር የቻሉትን ሁሉ ግፍ ፈፅመውብናል ነው ያሉት።

የመከራውን ፍፃሜ የሚመኝ በችግሮቹ ተደናቅፎ አይወድቅምና የጀመርነውን የህልውና ትግል ዳር አድርሰን በአጠረ ጊዜ ጠላቶቻችንን ታሪክ የምናደርግበት ጊዜ ተቃርቧል ሲሉም በመልዕክታቸው አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.