Fana: At a Speed of Life!

የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ኃይል አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ኃይል አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ።

የማእረግ አሰጣጥ መርሃ ግብሩም የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት ተከናውኗል።

የማእረግ እድገቱ የተሰጣቸው የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ሃይል አባላት ነው።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ1936 ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የኢትዮጵያን የአየር ክልል በማስከበርና ለአገሩ ሉአላዊነት በመቆም የገዘፈ ታሪክ ያለው ተቋም መሆኑ እንደሚታወቅ ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.