በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሳይንስ የትምህርትና ባህል ተቋም መዝገብ (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል በዓል ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው የተለያዩ የማይዳሰሱ እና የሚዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ የሚገኘው ክብረ በዓሉ ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ በተጨማሪ ባህላዊ ክዋኔው የጎላ ነው፡፡
በትናንትናው ዕለትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና የእምነቱ አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የደመራ ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡
ከአዲስ አበባ በተጨማሪም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የደመራ ስነስርዓት መከናወኑ ይታወቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!