በድሬዳዋ ከተማ ዛሬ አዲሱ መንግስት ተመሰረተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ በሚያካሂደው የምስረታ ጉባኤው ለቀጣይ 5 ዓመታት ከተማዋን የሚመራ አዲስ አስተዳደር ተመስርቷል፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ለአዳዲስ ተመራጮች ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በአስተዳደሩ በሶስተኛው ዙር ለምክር ቤቱ ተወዳድረው ላሸነፉ 189 ተመራጮች ነው ስልጠናው የተሰጠው፡፡
በስልጠናው ÷ ተመራጮች ለቀጣይ የስራ ዘመናቸው የሚሆኑ ግብዓቶች እንዳገኙበት የምክር ቤቱ የህግ አወጣጥ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ ተፈሪ ፍቃደ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ከመንግስት አካላት ምን ይጠበቃል የሚለውን ጨምሮ ከባለፈው የምክርቤቱ አባላት የነበሩ ልምዶች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት በሦስተኛ ዙር 49ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል፡፡
በዚህም ጉባኤው የምክር ቤቱን አፈጉባኤዎች መርጧል፡፡
የከተማዋን ከንቲባም ሰይሟል፡፡
በተጨማሪም ጉባኤው÷ የካቢኔ አባላት ሹመትንም አጽድቋል፡፡
ትናንት ምሽት ለነባር የምክር ቤት አባላት ሽኝት መደረጉም ተገልጿል፡፡
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!