Fana: At a Speed of Life!

ፅንፈኛውን የቅማንት ኮሚቴ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጭልጋ ወረዳ እና የአይከል ከተማ ነዋሪዎች ፅንፈኛውን የቅማንት ኮሚቴ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡
በህዝባዊ ሰልፉ ላይም÷ የአማራና የቅማንት ህዝብ አንድ ነው፣ ከፋፋይ ሀሳብን እንቃወማለን፣ የሀገራችንን የውስጥና የውጭ ባንዳዎችን እንቃወማለን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተስተጋብተዋል፡፡
የቅማንት ህዝብ ከወንድም የአማራ ህዝብ ብሎም ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም የጁንታውን ሀገር የማፍረስ ሴራ በፅኑ እንቃወማለን ሲሉም የሰልፉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.