ሰሜን ኮሪያ ሃዉሶንግ 8 የተሰኘ ሚሳኤል አስወነጨፈች
አዲስ አበባ፣ መሰከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ ) ሰሜን ኮሪያ ሃዉሶንግ 8 የተባለዉን ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ ማስወንጨፏን አስታውቃለች፡፡
የመጠቀዉ አዲሱ ሚሳኤል በሃገሪቱ የ 5 ዓመት ወታደራዊ ዕቅድ ዉስጥ አንዱ እንደሆነ እና ይህም የሃገሪቱን ወታደራዊ አቅም እንደሚያጎለብት የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ አመላክቷል፡፡
ቀደም ሲልም ሃገሪቷ የሚሳኤል ነዳጅ አምፖሏን ይፋ ማድረጓ የሚታወስ ሲሆን÷ አሁን ያመጠቀችዉ ሃዉሶንግ 8 ሚሳኤልም 3ኛዉ የዓለማችን ግዙፍ ሚሳኤል መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሃገሪቷ ወታደራዊ አቅም ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን በሰሜን ኮሪያ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አንኪት ፖንዳ ገልጸዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የሰሜን ኮሪያ ተወካይ ኪም ሶንግ “እኛ ራሳችንን ለመከላከል እና ደህንነትን እና ሰላምን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ብሔራዊ መከላከያችንን እየገነባን ነዉ፣ ስለሆነም መሳሪያ የማጎልበት አቅማችንን ልንከለከል አይገባም ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!