ከውጭ የሚመጡ ምርቶች የጥራትና የተስማሚነት ማረጋገጫ የሚያገኙበት አሠራር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቶች ኤክስፖርት ከሚደረጉበት ሀገር ከመጫናቸው በፊት የጥራትና የተስማሚነት ማረጋገጫ የሚያገኙበት የአሠራር ፕሮግራም ይፋ ሆነ፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቶች ኤክስፖርት ከሚደረጉበት ሀገር ከመጫናቸው በፊት የጥራትና የተስማሚነት ማረጋገጫ የሚያገኙበት የአሠራር ፕሮግራም ይፋ ሆነ፡፡
በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍሬ ሕይወት ወልደ ሐና ይፋ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለችው ብርሃን ለሁሉ ብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እ.አ.አ. በ2025 35 በመቶ የሚሆኑ ዜጎችን ከብሔራዊ የኤሌክትሪክ አውታር ውጪ የኤሌክትሪክ ብርሃን ተዳራሽ ለማድረግ አቅዳ እየሠራች ነው፡፡
እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ በርካታ የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ሲሆን÷ እስካሁን ወደ ሕብረተሰቡ በተሰራጩ የሶላር ቴክኖሎጂ ዕቃዎች ዝቅተኛ ጥራትና አጭር የአገልግሎት ጊዜ ተጠቃሚዎችና አስመጪዎች ቅሬታ እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ÷ ምርቶች ኤክስፖርት ከሚደረጉበት ሀገር የጥራትና ተስማሚነት ማረጋገጫ የሚያገኙበት አሠራር ይፋ ሆኗል ብለዋል፡፡
ይህም ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶች እንዲገቡና ተስማሚ ባልሆኑ ምርቶች ከሚደርስ ኪሳራ ህብረተሰቡንም ሀገርንም መጠበቅ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቶችን ጥራትና የተስማሚነት ደረጃ እንዲያረጋግጡ ቢሮ ቬሪታስ እና ኮቴክና ከተሰኙ ሁለት ካምፓኒዎች ጋር በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አማካኝነት ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በመርሃ ግብሩ ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅትና ከሌሎች መንግስታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማቱ የመጡ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን÷ የተሳተፉ ሲሆን መድረኩ በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በአፍሪካ ክሊን ኢነርጂ፣ በዩኬ ኤድ እና ቴትራ ቴክ ትብብር የተዘጋጀ መሆኑን ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!