Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እየደረሰባት ያለውን ጫና ለመቋቋምና ያላትን እውነት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፋ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ እየደረሰባት ያለውን ጫና ለመቋቋምና ሃገሪቱ ያላትን እውነት ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ዳያስፖራዎች እየሰሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የ2014 ሩብ አመት የስራ አፈጻጸምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
ባለፉት 3 ወራት ዳያስፖራው ማህበረሰብ ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታ ትክክለኛ በሆነ መንገድ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘብ ከ500 በላይ መልእክቶችን በመቅረጽ የትዊተር ዘመቻ ማካሄድ መቻሉን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
ከዚህም ባለፈ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ የሆኑበት 13 ሰላማዊ ሰልፎች እንደተካሄዱም አንስተዋል።
በሌላ በኩል ሃገራዊ የልማት ስራዎችን ለማገዝ የሃብት ማሰባሰብ ስራ መሰራቱን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ፣ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ደግሞ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን ኢቢሲ ዘግቧል።
ከኢንቨስትመንት ስራዎች ጋር በተያያዘ በ12 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ካፒታል 159 ፕሮጀክቶች ፍቃድ ማግኘታቸውንም ዋና ዳይሬክተሯ አንስተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.