አገር አቀፍ የመንገድ ደህንነት የህግ ማሻሻያ ማዕቀፍ ፕሮጀክት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር ደኅንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎትና የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር የሚያስችል ፕሮጀክት በይፋ አስጀመረ፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገረመው ዘለቀ÷ የህግ ማሻሻያ ማእቀፍ ፕሮጀክቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው የመንገድ ትራፊክ ህግ ክፍተት ላይ እየተሰራ ሲሆን÷ ቸግሮችም መለየታቸዉ ተገልጿል፡፡
የፌዴራል ትራንፖርት ባለስልጣን፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን፣ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የከተማ እና የክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ተቋማ በፕሮጀክቱ ትግበራ የላቀ ተሳትፎ የሚያደርጉ መሆናቸዉ ተጠቅሷል፡፡
በየደረጃው ያሉ አካላትም አዲስ በተሻሻላው የመንገድ ትራፊክ ህግ ላይ አስፈላጊውን ሙያዊ አስተያየት እና ግብዓት ከሰጡ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ይደረጋል መባሉን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!