ኢትዮጵያ የአስደማሚ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት- ዶ/ር ሂሩት ካሳው
አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የአስደማሚ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት ሲሉ የአዲስ አበባ የባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው ተናገሩ።
የኢሬቻ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በፌስቲቫሉ ላይ የተገኙት ዶክተር ሂሩት ካሳው÷ ህዝቦች ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው ለማቆየት ዋጋ ከፍለዋል ብለዋል።
ኢሬቻን የኦሮሞ ህዝብ ለብዙ አመታት ጠብቆ አቆይቷል ያሉም ሲሆን ÷አዲሱ ትውልድ ይህንን የማስቀጠል ሃላፊነት አለበት ብለዋል።
ኢሬቻ በህዝቦች መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠነክር በመሆኑ ለዘላቂነቱ መስራት ይገባል ሲሉም በመድረኩ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ይበልጥ በርካታ የአደባባይ በዓላት አሏት ያሉት ሃላፊዋ÷ይህም በህዝቦች መካከል ትስስርን በማምጣት ጉልህ ጠቀሜታ አለው ነው ያሉት።
የጠቀሜታው ተጋሪ ለመሆን ግን ይበልጥ ማስተዋወቅና የቱሪዝም ገበያው ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል ዶክተር ሂሩት፡፡
እንደ ኢሬቻ ያሉ ውድ እሴቶች ከትውልድ ትውልድ እንዲቀጥል ሃላፊነትን መወጣት እንደሚገባም ተናግረዋል።
ባህላችን የአንድነት መተባበራችን ማህተም ነው፤ ይህንን ለማጎልበት መንግስት በቀጣይ ከአምስቱ የልማት ምሶሶች አንዱ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነም ነው ያስታወቁት።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!