Fana: At a Speed of Life!

ኢሬቻ ወንድማማችነትን በማጠናከር ቁልፍ ሚና አለው- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ የፍቅርና የሰላም በዓል ነው፤ ወንድማማችነትን፣ ሕብረብሔራዊነትን በማጠናከርም ቁልፍ ሚና አለው ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
በመዲናችን አዲስ አበባ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ በዓል ለከተማችን ተጨማሪ ድምቀት እና የቱሪዝም መስህብ ነውም ብለዋል፡፡
ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው፤ ይህንን በዓል ስናከብር በሰላም እንድናከበር ህይወታቸውን በመስጠት ሀገር ያቆሙ ጀግኖችን ምንጊዜም በማመስገን እና በማስታወስ ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ኢሬቻ ክረምቱ በበጋ የሚተካበት ብቻ ሳይሆን ወደ ተስፋ መሻገሪያ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በአዲስ መንግስት ምስረታና በፈተናዎች ውስጥ ሆነን መከበሩ ደግሞ ልዩ ያደርገዋልም ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡
የኢሬቻን የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የይቅርታ መገለጫዎችን በመጠቀም በሁለንተናዊ መልኩ ፈተናዎቿን ድል የነሳች አገር እንገነባለን ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.