Fana: At a Speed of Life!

በቡሌ ምርጫ ክልል የምርጫ ውጤት ተለጠፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጌዴኦ ዞን በቡሌ ምርጫ ክልል ትላንት የተካሄደው ምርጫ ውጤት ተለጥፎ ቁሳቁስ የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቆ ቁሳቁስ እየተሰበሰበ በመሆኑ ደስ ብሎናል፤ ፍትሃዊነቱንም አረጋግጠናል ሲሉ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡
ትላንት ድምፅ የሰጡና ዛሬ ውጤቱንም የተመለከቱ ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ ምርጫው ታሪካዊና ፍፁም ፍትሃዊ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
በቡሌ ምርጫ ክልል በሚገኙ 83 የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ተለጥፎ ህብረተሰቡ እየተመለከተ መሆኑም ነው የተገለፀው፡፡
ተወዳደሪ ፖርቲዎችም ውጤቱን በፀጋ እንዲቀበሉ መራጮች አሳስበዋል፡፡
በታሪክነሽ ሴታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.