Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙ አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ፡፡
ፕሬዚዳንቷ በኢትዮጵያ የተሾሙ የታይላንድ ፣ የኒውዝላንድ ፣ የዴንማርክ ፣ የጅቡቲ ፣ የአውስትራሊያ ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የግብጽ አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ነው የተቀበሉት፡፡
በዚህ ወቅት የኢትዮጵያን ወቅታዊ እና ተጨባጭ ሁኔታ ለአምባሳደሮቹ አብራርተዋል።
እንዲሁም ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ÷ ኢትዮጵያም ከአውሮፓ ህብረትም ሆነ ከየሀገራቱ ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸው ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.