Fana: At a Speed of Life!

በሪፎርሙ ሀገርን እና ሕዝብን ከተለያዩ ጥቃቶች መጠበቅ የሚያስችለን አቋም ላይ ደርሰናል ሲል የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ በሪፎርሙ ሀገርን እና ሕዝብን ከተለያዩ ጥቃቶች መጠበቅ የሚያስችለው አቋም ላይ መድረሱን ገለጸ።
የፌዴራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት፣ ከመከላከያ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት አጠቃላይ በሪፎርሙ የደረሰበትን ደረጃ ለዕይታ አብቅቷል።
የፌዴራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት፣ ከመከላከያ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በተናበበ መልኩ ኢትዮጵያን ከተለያዩ ጥቃቶች ለመጠበቅ የሚያስችል አቋም ላይ መደረሱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገልጸዋል።
በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል፣ ከነገ በስቲያ በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል እና ሰኞ ዕለት የሚካሄደው ታሪካዊው የመንግሥት ምሥረታ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ሥራው አስተማማኝ እንዲሆን የሚያስችል በቂ ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቀዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ፤ በቀጣይም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አሁን በሰው ኃይል እና በትጥቅ የደረሰበትን ዘመናዊነት በማሳደግ በአፍሪካ በፖሊስ ብቃት ከሚጠቀሱ ሀገራት ከ1 እስከ 10 ባለው ደረጃ ውስጥ ለመሰለፍ የሚያስችለውን ሥራ እየሠራ ነው ብለዋል።
ዛሬ በመስቀል አደባባይ የታየው የሰው ኃይል እና ዘመናዊ የትጥቅ ትዕይንት መንግሥት ለኮሚሽኑ ሪፎርም ባደረገው ልዩ ትኩረት የተገኘ ውጤት መሆኑን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.