Fana: At a Speed of Life!

የህልውናውን ጦርነት ከመመከት ባሻገር ድህነትን መከላከል ለነገ የማይባል ተግባር ነው – ዶ/ር አስራት አፀደወይን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተከፈተብንን የህልውና ጦርነት ከመመከት ጎን ለጎን ረሀብንና ድህነትን ከወዲሁ መከላከል ለነገ የማይባል ተግባር ነው ሲሉ የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ገለጹ፡፡
በጎንደር ከተማ የገጠር ቀበሌዎች የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት የዘማች አርሶ አደር የደረሱ ሰብሎችን ሰብስበዋል፡፡
ከዛሬ ጠላታችን ባልተናነሰ የነገ ጠላታችን ረሃብ እንዳይሆን ከወዲሁ ለመከላከል ዩኒቨርሲቲያችን የተለያዩ የግብርና ጽንሰ ሐሳቦችን ይዞ እየሠራ ነው ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከዚህ ቀደም በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በጥናትና ምርምር፣ በተንቀሳቃሽ ህክምና አገልግሎት እና በተለያዩ ማህበረሰብ አገልግሎቶች ከፈትኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመው÷ ሰሞኑንም የደረሱ የዘማች ቤተሰብ ሰብሎችን እየሰበሰበ ይገኛል ብለዋል።
የዛሬ የዘማች አዝመራ መሰብሰብ ሥራ ለሦስተኛ ጊዜ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አስራት÷ ባለፉት ሁለት ዙሮች ከሁለት ሄክታር በላይ የጤፍ አጨዳ ሥራ ተከናውኗል፤ በቀጣይም የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ይህን ሂደት ለየት የሚያደርገው የቻሉ ሠራተኞች በጉልበታቸው ሲያጭዱና ሲሰበስቡ፣ በተለያዩ ምክንያቶች አዝመራ መሰብሰብ ያልቻሉ ደግሞ የቀን ሠራተኞችን ቀጥረው አሰርተዋል ብለዋ ዶ/ር አስራት፡፡
የሁልጊዜ የሕዝብ አገልጋይ ለሆነው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ፕሬዘዳንቱ ምስጋና አቀርበዋል።
በኤልያስ አንሙት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.