የጅግጅጋ ነዋሪዎች ለተፈናቃዮች ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ አደረጉ
“ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል ሀሳብ የጅግጅጋ ነዋሪዎች በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉም ከባለሀብቶች እና ከአብያተ ክርስቲያናት የተሰበሰበ ሲሆን÷ የንጽህና መጠበቂያ፣ አልባሳትና የተለያዩ የምግብ ምርቶችን ያካተተ ነው፡፡
አጠቃላይ ግምቱም 4 ሚሊየን ብር ነው ተብሏል፡፡
በድጋፍ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የሶማሌና የምስራቅ ሀረርጌ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ መቃርዮስ ÷ በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰው ጥቃት የሁሉንም ልብ የሚሰብር በመሆኑ ከጎናችሁ መሆናችንን ለማሳየት ነው ድጋፉን ይዘን እዚህ የተገኘነው ብለዋል፡፡
ወራሪው ሀይል እስከሚደመሰስም አጋርነታችን ይቀጥላል ነው ያሉት።
ድጋፉን የተረከቡት የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ በበኩላቸው÷ አጋርነታችሁን ለማሳየት ላደረጋችሁት ድጋፍ በህዝባችን ስም ምስጋናችችንን እናቀርባለን ብለዋል።
በሰላማዊት ሙሉነህ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!