የኦሮሚያ ክልል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲስ ለተመሠረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች እና ወደ አመራርነት ለመጣችሁ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።
የኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመጣል በምታደርገው ጥረት ውስጥ እናንተ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የክልልነት ጥያቄያችሁ አወንታዊ ምላሽ እንዲያገኝ ያደረጋችሁት ጥረት እንደ መሰረት ድንጋይ የሚታይ እና እንደ ማሳያም የሚነሳ እንደሚሆን ክልላችን በጽኑ ያምናል ብሏል በመልዕክቱ፡፡
በቀጣይም የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና መላው የክልላችን ህዝብ ክልሉ በሁለንተናዊ መልኩ ተጠናክሮ እና በሁለት እግሩ ቆሞ የክልሉን ህዝቦች ማገልገል በሚችለው ልክ እና መጠን እስከሚያገለግል እና የኢትዮጵያ ብልጽግና እስከሚረጋገጥ ድረስ በሁሉም መንገድ ከጎናችሁ እንቆማለንም ብሏል።
የህዝቦቻችንን የአብሮነት ታሪክ በሌላ ቃልኪዳን እናጸናለንም ነው ያለው ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት።
የህዝቦቻችንን የአብሮነት ታሪክ በሌላ ቃልኪዳን እናጸናለንም ነው ያለው ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት።
የክልላችን መንግስት እና ህዝብ ከዚህ ቀደም ከሌሎች ክልሎች ጋር ስናደርገው እንደነበረው ሁሉ ከአዲሱ ክልል ጋርም በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር በጽኑ ወዳጅነት ፣ አብሮነት ፣ ትምምን እና ጥልቅ ፍቅር አብረን የምንቀጥል መሆናችንን እንገልጻለንም ነው ያለው፡፡
አሁንም በድጋሚ በአገራችን 11 ኛ ክልል ሆኖ ለተመሰረተው የደቡብ ምእራብ ህዝቦች ክልል ህዝቦች እና አመራሮች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ደስታ በመግለጽ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!