ታሪክ ሳናበላሽ ፤ታሪካችንን በደማቅ ቀለም ከትቦ እና የማያልፍ ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ትልቅ ዕድል ነው-ከንቲባ አዳነች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ከመዲናዋ አርሶ አደሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ከንቲባ አዳነች ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን የህልውና ጦርነት በድል እንድትወጣ ለመከላከላከያ ሰራዊቱና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ የከተማ አርሶ አደሮች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አርሶ አደሮቹ የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ ከማስጠበቅ በተጨማሪ ልጆቻቸውን ወደ ግምባር መርቀው በመላክ የህልውና ዘመቻውን በድል እንድንወጣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡
ታሪክ ሳናበላሽ ፤ ታሪካችንን በደማቅ ቀለም ጽፎ እና የማያልፍ ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ትልቅ እድል ነው ያሉት ከንቲባዋ÷ ለዚህም የከተማ አርሶ አደሩ የአዲስ አበባን ዙሪያ በንቃት በመጠበቅ እንዲሁም ለአገር መከላከያ ሰራዊቱ እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የከተማዋ አርሶ አደሮች በበኩላቸው÷ከከተማዋ ከንቲባ የቀረበላቸውን የእናት አገር ጥሪ በመቀበል ኢትዮጵያ ወደ ተረጋጋ ሰላም እስክትመለስ ድረስ ከመንግስትና ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመሆን የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ለመከላከያ ሰራዊቱና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደርጉትን ድጋፍ ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም መናገራቸውንም ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!