Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጥላሁን ከበደ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጂዎችን ለማቋቋም የተጀመሩ ስራዎችን ገመገሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የመሬት መንሸራተት በደረሰው አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተጀመሩ ስራዎችን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል…

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ በጉባዔው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የአስፈፃሚና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2016 ዓ.ም የአፈፃፀም ሪፖርትን እያቀረቡ…

ሚኒስቴሩ ለጎፋ ዞን 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከ6 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብሩ በጥሬ…

በግብርናው ዘርፍ የሚገኙ ፕሮግራምና ፕሮጀክቶች የዘርፍን ሽግግር ለማፋጠን ትልቅ ሚና አላቸው – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርናው ዘርፍ የሚገኙ ፕሮግራምና ፕሮጀክቶች የዘርፍን ሽግግር ለማፋጠን ትልቅ ሚና አላቸው ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች፣ የክልል ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የምግብ…

የጋምቤላ ክልል የሕብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳቸውን ለይተው ለኮሚሽኑ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ቀናት በጋምቤላ ክልል ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡ ከሐምሌ 22 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ከ14 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች አጀንዳቸውን አጠናክረው…

በመዲናዋ በምርቶች ላይ አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ አካላት ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ይደረጋል – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርቶች ላይ አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩና ምርት በሚሰውሩ አካላት ላይ ጠንካራ ቁጥጥርና ሕግ የማስከበር ሥራ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከንግድ ማህበረሰብ አባላትና ከከተማ አስተዳደሩ…

በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬና መዲና ኢሳ ለፍፃሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሎምፒክ 5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬና መዲና ኢሳ ለፍፃሜ አልፈዋል፡፡ ምሽት 1 ሠዓት ከ10 ላይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ተካሂዷል፡፡ በዚህም በምድብ አንድ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 14፡57፡84፣…

በአዲስ አበባ አንድ ባለሀብትን በማገት 20 ሚሊየን ብር የተቀበሉ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አንድ ባለሀብትን በማገት 20 ሚሊየን ብር የተቀበሉ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። አጋቾቹ 20 ሚሊዮን ብር የተቀበሉት 100 ሚሊዮን ብር ካልከፈላችሁ በሚል ከብዙ…

መንግስት በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ የአቅርቦትና የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር በቂ ዝግጅት አድርጓል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር መመሪያ መውጣትን ተከትሎ በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ የአቅርቦትና የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት መንግስት በቂ ዝግጅት ያደረገ መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)…

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ቦረና ዞን የፊና ቡርቂቱ ፕሮጀክት የስራ ሂደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ቦረና ዞን የፊና ቡርቂቱ ፕሮጀክት የስራ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ከርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተጨማሪ በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ፣…