Fana: At a Speed of Life!

ብልፅግና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገሩ ባሕር ዳር ሕያው ምስክር ናት – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገሩ ባሕር ዳር ሕያው ምስክር ናት አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ…

ያላ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለግዙፍ አግሮ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት በር ከፋች ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በጋሞ ዞን የተገነባውን ያላ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል። ርዕሰ መስተደድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ፋብሪካው ለአካባቢው አርሶ አደሮችና ወጣቶች…

ብልፅግና ፓርቲ በአርባ ምንጭ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልፅግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር አካሂዷል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷…

የቀጣናው ኃይሎች ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች ጋሻ ሊሆኑ አይችሉም – ኢራን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የቀጣናው ኃይሎች ከዚህ በኋላ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮችን ከቴህራን አጸፋ ሊከላከሉ አይችሉም አሉ። የአሜሪካ ኃይሎች፣ የጦር ሰፈሮች እና በመካከለኛው ምስራቅ ያላት ፍላጎቶች ከአሁን በኋላ ከጥቃት…

ለሀገር ዕድገት ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ የተዘጋጁት የሶዶ ከተማ ነዋሪዎች…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ልማትና ዕድገት የሚበጀውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል አሉ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች፡፡ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች፥ ቤተሰቦቻቸውን ጭምር በማንቃት…

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የተመረቀው ግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ምን አይነት ሴራሚኮችን ያመርታል፡-

‎ፋብሪካው የተገነባው በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ነው፣ መሰረት ልማቱ በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን÷ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ የሴራሚክና የፖርሲሌን ንጣፎችን ያመርታል፣ ፋብሪካውን ከዕቅድ ጀምሮ እስከ መሬት…

ለመከላከያ ሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች የተገነቡ 232 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀዋሳ ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ቋሚ ሲቪል ሠራተኞች የተገነቡ 232 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) በተገኙበት ነው በይፋ ተመርቀው…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን በዛሬው ዕለት መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካልና የ“ኢትዮጵያ…

በቻይና በድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ማዕከል ላይ በደረሰ ፍንዳታ የ90 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜናዊ ቻይና ሻንሺ ግዛት በሚገኝ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማጣሪያ ማዕከል ላይ በደረሰ የጋዝ ፍንዳታ ቢያንስ የ90 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ አደጋው በቶንግዡ ግሩፕ በሚተዳደረው ሊውሼንዩ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማጣሪያ ማዕከል ውስጥ የተከሰተ…

የዓድዋ የገበያ ማዕከልና የትራንስፖርት ተርሚናል ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ መሃል ፒያሳ የተገነባው የዓድዋ የገበያ ማዕከልና የትራንስፖርት ተርሚናል በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ፒያሳ በቀድሞ አጠራሩ “ዶሮ ማነቂያ”…