Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጉብኝት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት እውቅና የሰጠ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት እውቅና የሰጠ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ሳምንታዊ…

ሩሲያ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

ተተኩሶአዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በተሳካ ሁኔታ ማከናወኗን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚሳኤሉ ከደቡባዊ ሩሲያ ካፑስቲን ያር ተተኩሶ በካዛኪስታን ሳሪ ሻጋን በሚገኘው ክልል ውስጥ በታቀደለት መልኩ ማረፉ ተገልጿል።…

በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ። በውይይቱ አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ…

የቅባት እህል አምራቾችን ከዘይት አምራቾች ጋር የሚያገናኝ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅባት እህል አምራቾችን ከዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚያገናኝ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው። ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ግብርና ሚኒስቴር እና ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ÷ የቅባት እህል አመራረት፣…

የጋምቤላ ክልል አልሚዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠራ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያየ የኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የጋምቤላ ክልል መንግስት ገለጸ፡፡ የክልሉን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና የዘርፉን ማነቆዎች ለመፍታት ያለመው ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር…

በመዲናዋ ያለውን የገበያ ሁኔታ ለማረጋጋት በቅንጅት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና የአዲስ አባባ ንግድ ቢሮዎች መጪዎቹን በዓላት መሰረት በማድረግ በመዲናዋ ያለውን የገበያ ሁኔታ ለማረጋጋት በጋራ እየሠሩ መሆኑን ገለጹ፡፡ በዚሁ መሰረት በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ዩኒየን አማካኝነት ከ62 ሺህ ኩንታል በላይ እህል በአዲስ…

ልዩ ኃይልን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልል ልዩ ኃይልን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በተዘጋጀው የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ በአዲስ አበባ ውይይት ተካሄደ፡፡ ውይይቱ የተካሄደው÷ የሀገር መከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣…

ሕዝበ ሙስሊሙ ከተቸገሩት ጎን እንዲቆም ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ሙስሊሙ እንደ ወትሮው ሁሉ ከተቸገሩት ጎን መቆሙን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ጠየቀ፡፡ 3ኛው ዙር ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ ስርዓት “ኢፍጣራችን ለወገናችን” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡…

ቻይና በታይዋን ዙሪያ ወታደራዊ ልምምድ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ጦር በዛሬው ዕለት በታይዋን አቅራቢያ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ወታደራዊ ልምምድ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ በልምምዱም የውጊያ ዝግጁነት ቅኝቶች እና ወታደራዊ ስልጠናዎች መካሄዳቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡ ልምምዱም “ታይዋን እና ውጫዊ…

እንደ ሀገር እየታረሰ ያለው መሬት 16 ሚሊየን ሔክታር ብቻ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ሊታረስ ከሚችለው 74 ሚሊየን ሄክታር ውስጥ እየታረሰ ያለው 16 ሚሊየን ሔክታር መሬት ብቻ መሆኑ ተመለከተ፡፡ የአፈር አሲዳማነትን በማከም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡ በውይይቱ…