Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል የሴቶች ውድድር የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ በተካሄደው 3 ሺህ ሜትር መሠናክል የሴቶች ውድድር አትሌት ዓለምናት ዋለ ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች፡፡ በዚሁ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት መሠረት የሻነህ አራተኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት…

እስከ 470 ሚሊዮን ዶላር በሚደርስ ወጪ የጠጠር መንገድና ድልድዮች እንደሚገነቡ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪዎቹ 5 ዓመታት እስከ 470 ሚሊዮን ዶላር በሚደርስ ወጪ የጠጠር መንገድና ድልድዮች እንደሚገነቡ የከተማና መሰረተልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ መንገዶቹ የሚገነቡት በገጠር መንገድ ተደራሽነትና ትስስር ፕሮግራም ነው ተብሏል ። የከተማና መሰረተ…

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጁ ዓላማ በሕግ የሚመራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማስቻል መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ዓላማ ጤናማ፣ ፍትሐዊ እና በሕግ የሚመራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማስቻል መሆኑን የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ÷ ሕጉ አራት…

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታ ወርቅ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የእርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች፡፡ ዛሬ ረፋድ የተካሄደው የ20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር በአትሌት ስንታየሁ ማስሬ እና ምስጋና…

በቤንች ሸኮ ዞን ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በቤንች ሸኮ ዞን ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባውን የፔቱ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት መረቁ፡፡ ፕሮጀክቱ በዞኑ ግዲ ቤንች ወረዳ የሚገኙ የጻት እና ዲዙ…

ፈረንሳይ፣ እንግሊዝና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቃቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል የሚያስችሉ ጠንካራ ፉክክር የሚጠብቃቸው አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህ መሠረትም ምሽት 1 ሠዓት ላይ በቡድን አራት የተደለደሉት ፈረንሳይ ከፖላንድ እንዲሁም ኔዘርላንድስ…

ከ247 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 247 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ዕቃዎቹ የተያዙትም ከሰኔ 7 እስከ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገ ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚሁ መሠረትም 233 ነጥብ 8 ሚሊየን…

የድምፅ ኮሮጆዎች ከምርጫ ጣቢያ ወደ ምርጫ ክልል ጽ/ቤት ገብተዋል- የሆሞሻ ምርጫ ክልል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ዙር ቀሪ ሀገር አቀፍ ምርጫ መጠናቀቁን ተከትሎ የድምፅ ኮሮጆዎች ከምርጫ ጣቢያዎች ወደ ምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት መግባታቸውን የሆሞሻ ምርጫ ክልል ገለፀ። የሆሞሻ ምርጫ ክልል ኃላፊ አዲሱ ገዳፌ እንዳሉት÷ በምርጫ ክልሉ ውስጥ የድምፅ አሰጣጡና…

ተረጂነትን ለማስቀረት አመራሩ በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅበታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በማልማት ተረጂነትን ለማስቀረት የጀመረችውን ግብ ለማሳካት አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሠራ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት"…

ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ወጣቶች ለዘላቂ ሠላምና አብሮነት እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ። "የሰላም ባህልና አመለካከትን የመገንባት እና የመምራት ክኅሎት" በሚል መሪ ሐሳብ ከክፍለ ከተሞች ለተውጡ ወጣች በሰላም ላይ የታኮረ…