Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጂቡቲ 2ኛ ሰርኪዩት የኃይል ትስስር መስመር ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ- ጂቡቲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ሁለተኛ ሰርኪዩት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ…

በደቡብ ክልል በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ችግሮች ለተፈናቀሉ ወገኖች የ320 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በደቡብ ክልል በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ ችግሮች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም የ320 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ድጋፉን ለደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ…

ፈረንሳይ የቅዱስ ላሊበላ አብያተክርስቲያትን ለማደስ የ5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ መንግሥት የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን ለማደስና ለመጠበቅ አገልግሎት የሚውል የ5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ፡፡ የዛሬው የድጋፍ ስምምነት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከአራት…

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚውን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ27ኛው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸነፈ፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ብቸኛ ጎል መስፍን ታፈሰ በ20ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ…

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ 3 ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ ሦስት ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል፡፡…

24ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 24ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡ በጉባኤው የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች እና በየደረጃው ያሉ የክልል የሥራ…

ለመጠጥ ውሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን ፕሮግራም ውጤታማነት የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተቋማት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሠራር የመጠጥ ውሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ማስቻሉ ተገለጸ፡፡ በጋና አክራ እየተካሄደ በሚገኘው “All System Go Africa” ሲምፖዚየም ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የውሃና ኢነርጂ…

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው÷ ከ1ኛ መደበኛ ስብሰባ የተሸጋገሩ ሦስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡ በተጨማሪም የቋሚ ኮሚቴዎችን…

በክልሎች ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ በቀረበ ሠነድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች ''በደም የተከበረ በላብ የታሰረ'' በሚል መሪ ሐሳብ ዘላቂ ሰላምና ቀጣይነት ያለው ዕድገት የማረጋገጥ ውጥኖች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡ እስካሁን ድረስ በጋምቤላ እና ሐረሪ ክልሎች ውይይቱ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ በሶማሌ…

በትግራይ ክልል ከአሸባሪው ቡድን ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰብዓዊ እርዳታ በተሣለጠ መንገድ እንዲደርስ በቂ ዝግጅት ተደርጓል – ለሰብዓዊ ድጋፍ…

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰብዓዊ እርዳታ በተሣለጠ መንገድ እንዲደርስ በቂ ዝግጅት መደረጉን ለሰብዓዊ ድጋፍ የተዋቀረው ኮሚቴ አስታወቀ። የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦትን ለማሳለጥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከውጭ…