Browsing Category
የሀገር ውስጥ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሱዳን ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ሱዳን ገብተዋል፡፡
ጉዞው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሱዳን መረጋጋት የሚያከናውኑት ጥረት ቀጣይ ርምጃ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ የንግድ ሥርዓትን ተላልፈው የተገኙ 21 ሺህ የንግድ ተቋማት ታሸጉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ ሥርዓትን ተላልፈው የተገኙ 21 ሺህ የንግድ ተቋማት እንደታሸጉ፣ ምርታቸው ከገበያ እንዲሰበሰብና ሌሎች እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ገለጸ።
የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት…
በትግራይ ክልል ለ2013 እና 2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መሰጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ፈተና መስጠት ተጀመረ፡፡
ፈተናው በክልሉ መቐለ፣ አኽሱም፣ ዓዲ-ግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች…
የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
እስከ አሁን ከእሪ በከንቱ በፒያሳ አራት ኪሎ ያለውን የኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች የኮሪደር ልማት…
እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች በአዲስ አበባ እግር ኳስ መሰረተ ልማት መስፋፋት ላበረከቱት አስተዋፅኦ…
1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ 1 ሺህ 095 ወንዶችና 79 ሴቶች ሲሆኑ÷ከእነዚህም መካከል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 21 ታዳጊዎች ይገኙበታል።…
አውቶብሶችን የሚገጣጥም ኩባንያ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ564 ሚሊየን ብር የኢንቨስትመንት ካፒታል የተለያዩ አውቶብሶችን ለመገጣጠም ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡
ገሊላ ማኑፋክሪንግ የተባለ ሀገር በቀል ኩባንያ በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ31ሺህ ካሬ ሜትር የለማ…
የወጣት ሴቶችን የዲፕሎማሲ ተሳትፎ ለማበረታታት በትኩረት መስራት ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወጣት ሴቶችን የዲፕሎማሲ ተሳትፎ ለማበረታታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
ፕሬዚዳንቷ በሁለተኛው "የሴቶች በዲፕሎማሲ ዓለም አቀፍ ቀንን" አስመልክቶ በተዘጋጀ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።…
በቄለም ወለጋ ላሎ ቂሌ ከተማ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቄለም ወለጋ ዞን ላሎ ቂሌ ከተማ ከ121 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡
ፕሮጀክቱን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ መርቀው ሥራ አስጀምረውታል።…
ለአልሸባብ ድጋፍ በማድረግና መረጃ በማቀበል ወንጀል የተከሰሱ 9 ግለሰቦች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአልሸባብ የሽብር ቡድን የጦር መሳሪያ መሬት ውስጥ በመደበቅ፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እና መረጃ በማቀበል ወንጀል የተከሰሱ ዘጠኝ ግለሰቦች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ።
በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ የሽብር ወንጀል ተግባር ሲፈጽሙ በጸጥታ አካላት የተያዙ…