Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በብሪክሱ መድረክ ተባብሮ የመስራት ችሎታዋንና ዓለም አቀፋዊ አጋርነቷን ማስመስከር ችላለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ የተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም በስኬት ተጠናቋል፡፡ የጉባኤው ተሳታፊዎችም በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ 24 ነጥቦችን የያዘ የአቋም መግለጫ በማውጣት ለስኬታማነቱ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።…

እስከ ሰኔ 9 ቀን 2016 ድረስ 13 ነጥብ 63 ሚሊየን ሔክታር በባህላዊና በትራክተር ታርሷል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016/17 ምርት ዘመን የመኸር ወቅት እስከ ሰኔ 9 ቀን 2016 ድረስ 13 ነጥብ 63 ሚሊየን ሔክታር በባህላዊና በትራክተር መታረሱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ዘንድሮ በመስኖ ስንዴ ልማት 3 ሚሊየን ሔክታር በማረስ 120 ሚሊየን ኩንታል…

ለጤና ጠንቅ የሆነ ህገ ወጥ ጨው አከማችተው የተገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች በገንዘብና በፅኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ 34 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ለጤና ጠንቅ የሆነ ህገወጥ ጨው በመጋዘን አከማችተው የተገኙ 2 ድርጅቶችና 3 ግለሰቦች በገንዘብና በፅኑ እስራት ተቀጡ። የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ነው…

በአማራ ክልል ለተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች የተሰጠው ምላሽ የከፋ ችግር እንዳይደርስ አድርጓል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ለተከሰቱ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት የተሰጠው ፈጣን ምላሽ የከፋ ችግር እንዳይደርስ ማድረጉን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን ገለጹ፡፡ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ…

በሁመራ እና አካባቢው የተቋረጠውን ኃይል መልሶ ለማገናኘት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁመራ እና አካባቢው በተፈጥሯዊ አደጋ ምክንያት የተቋረጠውን ኃይል መልሶ ለማገናኘት የሚያስችል ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ፡፡ ከሽሬ- ሁመራ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ተሸካሚ የብረት…

የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የ2016 የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ…

ክልላዊ የኢንቨስትመንት ፎረም በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ የሆነው የኢንቨስትመንት ፎረም በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ፀሐይ ወራሳ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ…

የሐረሪ ክልል ያልተገባ ክፍያ በሚጨምሩ ት/ቤቶች ላይ ርምጃ እወስዳለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመመሪያ ውጭ ያልተገባ የትምህርት ቤት ክፍያ በሚጨምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ርምጃ እንደሚወስድ የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በ2017 የትምህርት ዘመን ከትምህርት ቤት ክፍያ ጋር ተያይዞ ጭማሪ ያደረጉና ያላደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች…

አቶ እንዳሻው በሃድያ ዞን የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በክልሉ ሃድያ ዞን የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን መርቀዋል፡፡ በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፍቃዱ እና…

ታማሚ አሳፍሮ ወደ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተገልብጦ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዳሰነች ወረዳ ታማሚ አሳፍሮ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተገልብጦ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ አደጋው የደረሰው በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ አርጎ ቀበሌ…