Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

በአፋር የቱሪዝም ሃብትን በማልማትና በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ያለውን የቱሪዝም ሀብት በማልማትና በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ በክልሉ ያሉ የቱሪዝም ሃብቶችና ባህሎችን የማስተዋወቅ…

9ኛው አፍሪካ አቀፍ የወባ ትንኝ ቁጥጥር ማኅበር ጉባዔ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው አፍሪካ አቀፍ የወባ ትንኝ ቁጥጥር ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔ እና ዐውደ - ርዕይ ተጠናቀቀ፡፡ ጉባዔው "በበሽታ ተኅዋስያን ላይ ከሚታዩ ሥጋቶች አንፃር ክትትልን እና ቁጥጥርን ማስተካከል"…

በኢትዮጵያና አልጄሪያ መካከል የቀጥታ የአውሮፕላን በረራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በአልጄሪያ መካከል የመጀመሪያው የቀጥታ በረራ ተደርጓል፡፡ የቀጥታ በረራውን በአልጀሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአልጀርስ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከአልጄሪያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዮሴፍ ቸርፋ እና…

ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ሰዎች ሕክምና የሚውል የወባ መድኃኒት ተሠራጨ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ሊያክም የሚችል የወባ መድኃኒት ባለፉት ሦስት ወራት መሠራጨቱን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ እንዲሁም ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ሊያክም የሚችል መድኃኒት በክምችት መኖሩን…

ኢትዮጵያ በቻይና እየተካሄደ በሚገኘው የቡና ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቻይና ሀንጆ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የቡና ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች፡፡ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፈረንጆቹ ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2023 በሚካሄደው "ኮፊ መንዝ ኦፍ ኤዥያ ጌም፣…

ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1868 በአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመልሰዋል፡፡ ከተመለሱት ቅርሶች መካከል የመድሃኒዓለም ታቦት፣ የልኡል ዓለማየሁ የጸጉር ዘለላ፣ ከብር የተሰሩና በነሃስ…

ጉቴሬዝ ተመድ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ "ሰላም ፣ብልፅግና፣ ለውጥና ዘላቂነት" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ከሚገኘው የተመድ 78ኛ…

ለግጭቶች እልባት በመስጠት ሰላምን እናጽና – የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግጭት ምክንያቶችን ለይቶ በማውጣት እልባት በመስጠትና ሰላምን በማጽናት በኩል ሁሉም ዜጋ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ በአጀንደ ልየታ ላይ የሚሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመምረጥ በጋምቤላ ከተማ ለሦስት…

በሸገር ከተማ በ16 ቢሊየን ብር ወጪ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ለገ ጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል። ፕሮጀክቶቹ 374 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን÷በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ዜጎች የተገነቡ ቤቶች፣…

ከ300 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ተደመሰሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ300 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አባላቱ መቁሰላቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። በሶማሊያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ ሃይል ለመቀየር ተልዕኮ ወደ ሚፈፀምበት ቦታ በተንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ…