Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአሜሪካ ግዛቶች በተከሰተ አውሎ ንፋስ 26 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ሚሲሲፒ እና አልባማ ግዛቶች በተከሰተ ከባድ አውሎ ንፋስ 26 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡ ባለፈው አርብ ጀምሮ የተከሰተው ከባድ አውሎ ንፋስ በሚሲሲፒ ግዛት 25 ሰዎችን ለህልፈት ሲዳርግ ከአልባማ ግዛት ደግሞ በአደጋው የአንድ ሰው…

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢራንን አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንትጆ ባይደን ኢራንን ክፉኛ አስጠንቅቀዋል፡፡ በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ዋሺንግተን “ከኢራን ጋር ግንኙነት አላቸው” ባለቻቸው ታጣቂዎች ተደጋጋሚ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል፡፡ ፕሬዚዳንት…

ሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ተሸካሚ የውሃ ውስጥ ድሮን ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያለው የውሃ ውስጥ ሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላን (ድሮን) ሙከራ ማካሄዳቸውን የሀገሪቱ የዜና ጣቢያ ገለጸ፡፡ የውሃ ውስጥ ድሮኑ ከ80 እስከ 150 ሜትር ባለ ጥልቀት ውስጥ በውሃ…

አሜሪካ በደቡብ ቻይና ባህር አዲስ የጦር ሰፈር ለመገንባት ማቀዷ ቻይናን አስቆጣ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በደቡብ ቻይና ባህር አቅራቢያ አዲስ የጦር ሰፈር ለመገንባት ማቀዷ ቻይናን አስቆጥቷል፡፡ አሜሪካ በፊሊፒንስ አቅራቢያ አራት አዳዲስ የጦር ሰፈሮችን ልትገነባ መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርከስ አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ…

የዓየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቋቋም በየዓመቱ 3 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም በየዓመቱ 3 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የብሪታኒያ የኃይል ሽግግር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ባወጣው ሪፖርት የዓለም ኢኮኖሚ ከካርበን ልቀት ነፃ መሆን የሚችልበትን አማራጮች ማመላከቱን ሲ…

ቭላድሚር ፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ የተለያዩ ሥምምነቶችን ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ የተለያዩ ሥምምነቶችን ተፈራረሙ።   ሥምምነቶቹ ሀገራቱ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በሳይንስ እና ወታደራዊ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክሩ ናቸው ተብሏል።…

ቻድ ከ400 በላይ የሚሆኑ አማፂያን በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ወሰነች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻድ ከ400 በላይ የሚሆኑ አማፂያን በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ መወሰኗን የሀገሪት ዐቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡ እስራቱ የተፈረደባቸው አማፂያን በፈረንጆቹ 2021 በቀድሞው የቻድ መሪ ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ግድያ ላይ የተሳተፉ ናቸው ተብሏል።…

በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ የ43 ሺህ ሰዎች ሕይወት ቀጥፏል – ጥናት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ አሁንም የቀጠለው ድርቅ ባለፈው ዓመት ብቻ የ43 ሺህ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ጥናት አመላከተ፡፡ በድርቁ ሳቢያ ሕይወታቸውን ካጡ ሰዎች ግማሽ ያኅሉ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች መሆኑን በእንግሊዝ የሚገኘው የለንደን የትሮፒካል ሕክምና…

ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው 104 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት ደርሶብኛል አለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት በፈረንጆቹ የካቲት 6 ላይ በቱርክ በተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 104 ቢሊየን ዶላር ገደማ ጉዳት መድረሱ ተነገረ፡፡ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ÷ እንዲህ ያለው አደጋ በራስ ዐቅም ብቻ የሚመከት ባለመሆኑ…

ሩሲያ እና ቻይና “መልካም ጎረቤታሞች” እና “የሚተማመኑ አጋሮች” ናቸው – ሺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ቻይና “መልካም ጎረቤታሞች” እና “የሚተማመኑ አጋሮች” ናቸው ሲሉ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡ ሺ ጂንፒንግ የሩሲያ ጉብኝታቸውን በጀመሩበት ወቅት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡…