Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

የዩክሬንን እህል የጫነችው መርከብ ቱርክ ወደብ ደረሰች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መርከቧ በትናንትናው ዕለት በቦስፎረስ ባህር ወሽመጥ አቅራቢያ ቱርክ ግዛትመድረሷ ተነግሯል። ራዞኒ የተሰኘችው መርከብ ከ26 ሺህ ቶን በላይ በቆሎ ወደ ሊባኖስ እና ትሪፖሊ ታደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል። የሩሲያ እና…

በፈረንጆቹ 2022 አጋማሽ በተፈጥሮ አደጋ ብቻ የ72 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ደርሷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2022 መጀመሪያ አጋማሽ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ አደጋዎች የተከሰተው አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ 72 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ አንድ ዓለም አቀፍ የሕይወት እና የጤና መድን ዋስትና ድርጅት አስታወቀ፡፡ ይህን ከፍተኛ ኪሳራ…

ቻይና የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ በደሴቷ ላይ ተከታታይና የተመረጡ ወታደራዊ እርምጃዎችን እወስዳለሁ አለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ በደሴቷ ላይ ተከታታይና የተመረጡ ወታደራዊ እርምጃዎችን እንደምትወስድ አስታወቀች። የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የቻይናን ተደጋጋሚ እና ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ወደጎን በመተው…

አፈ-ጉባዔ ፔሎሲ አወዛጋቢ የሆነውን የታይዋን ጉብኝት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ አወዛጋቢ ሆኖ የቆየውን የታይዋን ጉብኝታቸውን ጀምረዋል ። የፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት አስመልክቶ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ ጉብኝቱን በጥብቅ ማውገዙን ሲጂቲ…

ቻይና የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ እንደመግባት ይቆጠራል አለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን የሚያደርጉት ጉዞ በቻይና የውስጥ ጉዳይ እንደመግባት እንደምትቆጥር ቤጂንግ ገለፀች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ አፈ-ጉባዔዋ…

የአየር ንብረት ለውጥ በዚህ ከቀጠለ የሰው ልጅን ሊያጠፋ እንደሚችል አዲስ ጥናት አመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ በዚህ ከቀጠለ የሰው ልጅን ከምድረ ገጽ ሊያጠፋ እንደሚችል አዲስ ጥናት አመለከተ። የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ካልተቻለ በዚሁ ምክንያት የሰው ልጅ ከምድር ሊጠፋ እንደሚችል መታወቅ አለበት ሲል አዲሱ ጥናት…

የአልቃይዳው መሪ አይመን አል ዛዋህሪ ተገደለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የአልቃይዳውን መሪ አይመን አል ዛዋህሪ መግደሏን ገለፀች። ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይፋ እንዳደረጉት ኦሳማ ቢን ላደንን ተክቶ የሽብር ቡድኑን ሲመራ የነበረ አል ዛዋህሪ አፍጋኒስታን፣ ካቡል ውስጥ በድሮን በተፈፀመ ጥቃት ተገድሏል።…

ምድረ በዳውን መሬት ወደ ደንነት የቀየረው ቱርካዊ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርካዊው ሂክመት ካያ 30 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ምድረ በዳውን መሬት ወደ ደንነት መቀየር ችሏል፡፡ ቫይራል ባንዲት በተባለ መጽሄት ላይ በህትምት የወጣው ጽሑፍ እንደሚያስረዳው÷ ግለሰቡ ከቱርክ የደን አስተዳደርነት በጡረታ ቢገለልም በስራ ዘመኑ…

ፕሬዚዳንት ባይደን ስትራቴጂክ የጦር መሳሪያን በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋሽንግተን አዲሱን የስትራቴጂክ የጦር መሳሪያ ቅነሳ እና ቁጥጥር ማዕቀፍ በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ገለጸች። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአሥረኛው ከፀረ- የጦር መሳሪያ መስፋፋት ስምምነት የግምገማ ጉባኤ ቀደም ብሎ…

ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራችው ሲ-919  የመንገደኞች አውሮፕላን የሙከራ በረራውን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ለንግድ አገልግሎት የሚውል ሲ-919 ትልቅ የመንገደኞች አውሮፕላን የሙከራ በረራውን ማጠናቀቁን የቻይና የንግድ አውሮፕላኖች ኮርፖሬሽን አስታወቀ። ኩባንያው አውሮፕላን የማምረት ሥራውን በ2015 አቋርጦ የነበረ…