Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
በዩክሬን የጸጥታና ደኅንነትን ጉዳይ ላይ ሩሲያ ከማንም ጋር ለውይይት አልተቀመጠችም – ሰርጌ ላቭሮቭ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬን የጸጥታና ደኅንነትን ጉዳይ ላይ ሩሲያ ከየትኛውም ሀገር ጋር ለውይይት እንዳልተቀመጠች የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናገሩ፡፡
ሰርጌ ላቭሮቭ ከካዛኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙክታር…
ቻይና ታይዋንን በኃይል ለመያዝ ከሞከረች አሜሪካ ወታደራዊ ኃይሏን ትጠቀማለች -ፕሬዚዳንት ባይደን
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የታይዋን ደሴትን በኃይል ለመያዝ ከሞከረች አሜሪካ በቀጥታ ከቻይና ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ መሆኗን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ፡፡
ጆ ባይደን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋር በቶኪዮ ተገናኝተው በጋራ…
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ምክትል አዛዥ በታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ
አዲስ አበባ፣ግንቦት 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን አብዮታዊ ዘብ አባል እና ምክትል አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሰኢድ ሃዲ በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸው ተዘግቧል፡፡
ኮሎኔል ሰይድ ሆዳይ በኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ምክትል አዛዥ እና የውጭ ኦፕሬሽን ቡድን አባል ሲሆኑ፥ ቴህራን በሚገኘው…
በሣምንቱ ከ10 ሺህ ቶን በላይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ደርሷል – የዓለም የምግብ ፕሮግራም
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ሣምንት ከ10 ሺህ ቶን በላይ የምግብ እና የነፍሥ አድን አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡
የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶቹ በታጀቡ 163 የጭነት ተሽከርካሪዎች ሁለት ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዛቸውን…
በግጭት ምክንያት ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ100 ሚሊየን ማለፉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተመድ የሥደተኞች ኮሚሽን በግጭቶች አስገዳጅነት ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 ሚሊየን ማለፉን አስታወቀ፡፡
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተከሰተው ጦርነት የሥደተኞችን ቁጥር ከ100 ሚሊየን እንዲልቅ እንዳደረገው ኮሚሽኑ…
ሩስያ 963 አሜሪካውያንን እና 26 ካናዳውያንን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩስያ 963 አሜሪካውያን እና 26 ካናዳውያን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ማገዷን አስታወቀች፡፡
የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፥ 963 አሜሪካውያን መቼም ቢሆን ወደ አገሯ እንዳይገቡ ያገደች ሲሆን፥ እገዳው ከተጣለባቸው አሜሪካውያን መካከል…
ሩሲያ የዩክሬን የወደብ ከተማ የሆነችውን ማሪፖል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ወታደሮች የዩክሬን የወደብ ከተማ የሆነችውን ማሪፖል ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሸንኮቭ እንደገለጹት÷ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታዋ ከፍተኛ…
በአንድ ዓመት ውስጥ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በዓለም 60 ሚሊዮን ዜጎች ተፈናቅለዋል
አዲስ አበባ፣ግንቦት 12፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በፈረንጆቹ 2021 በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በዓለም ላይ 60 ሚሊዮን ዜጎች መፈናቀላቸውን ሪፖርቶች አመለከቱ፡፡
በ2021 በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ከተፈናቀሉ ሰዎች ከ18 ዓመት በታች የሆናቸው ዜጎች መሆናቸውን የውስጥ ተፈናቃዮች…
ቱርክ ዓለም ላይ የረሃብ አደጋ ሥጋት ሳይባባስ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እልባት እንዲሰጠው ጠየቀች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ - ዩክሬን ጦርነት በዓለም ላይ የተከሰተውን የረሃብ አደጋ እንዳያባብስ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትብብር እንዲሠራ ተመድ ባካሄደው የከፍተኛ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ቱርክ ጠየቀች፡፡
ተመድ "በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በድርጊት…
ቱርክ በስዊድን እና ፊንላንድ የኔቶ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምፅ እንዳይሰጥ አገደች
አዲስ አበባ፣ግንቦት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድን እና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ለመሆን ዛሬ በይፋ ባቀረቡት የጽሑፍ ማመልከቻ ላይ ቱርክ ባለመስማማቷ ሂደቱ እንዲታገድ ማድረጓ ተገለጸ።
ስዊድን እና ፊንላንድ የወታደራዊ ቃል ኪዳኑ…