Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ረጅም ርቀት ሚሳኤል ወደ ሩሲያ አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ፍቃድ መሠረት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ዩክሬን ወደ ብሪያንስክ ግዛት ካስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች አምስቱ በሩሲያ ጦር የከሸፉ መሆኑን…

አሜሪካ እስራኤል እና ሂዝቦላን ለማሸማገል ልዩ መልዕክተኛዋን ወደ ቤሩት ላከች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አሞስ ሆችስቴይን እስራኤል እና ሂዝቦላ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ለማሸማገል ቤሩት ገብተዋል፡፡ ልዩ መልዕክተኛው በቤሩት ቆይታቸው የሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ባለስልጣናት እንደሚኒጋግሩ ይጠበቃል፡፡…

ኢ-ፍትሐዊ አካሄዶችን ለመፍታት ቅንጅት ያስፈልጋል- ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም የሚታዩ ኢ-ፍትሐዊ አካሄዶችንና ጦርነቶችን ለመፍታት ሀገራት በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ አሳሰቡ። ፕሬዚዳንቱ በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር…

የሶማሊላንድ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የቀብር ሥነ-ስርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊላንድ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አሕመድ ሞሃመድ የቀብር ሥነ-ስርዓት ተፈጽሟል፡፡ በስነ-ሥርዓት ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህን…

በዴልሂ የተከሰተው የአየር ብክለት ከተማዋን ጨለማ አልብሷታል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ የተፈጠረው የአየር ብክለት ከተማዋን ጭጋግ በማልበስ ለእንቅስቃሴ አዳጋች ሁኔታ መፍጠሩ ተነገረ፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዴልሂ ከተማ የዓለም ጤና ድርጅት ለመተንፈስ አዳጋች ነው በሚል ካስቀመጠው የአየር ብክልት ደረጃ…

ባይደን በሩሲያ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ፈቃድ ሲሰጡ እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም – ቭላድሚር ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን ከአሜሪካ የተሰጣትን ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ሩሲያን ለመምታት እንድትጠቀምበት ፍቃድ ሰጥተዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሰጡት የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ተገቢ ምላሽ እንደምትሰጥ…

እስራኤል የሂዝቦላህን ዋና ቃል አቀባይ መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የሂዝቦላህ የሚዲያ ሃላፊ የሆነውን ሞሃመድ አፊፍ ሰይድን መግደሉን አስታውቋል፡፡ የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ቤሩት እና በሰሜን ጋዛ የሚፈጽመው የአየር ጥቃት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡ ጦሩ በዛሬው ዕለት…

ሩሲያ የዩክሬን የሀይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ደበደበች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት በይፋ ከተጀመረ ወዲህ ሩሲያ ከፍተኛ የተባለውን የአየር ድብደባ የዩክሬን የሀይል ማመንጫዎችን ኢላማ በማድርግ ጥቃት መፈጸሟ ተነገረ፡፡ በዚህም ሩሲያ 120 ሚሳኤሎችን እንዲሁም 90 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በሁሉም…

የዓለም ጤና ድርጅት የኩፍኝ በሽታ እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የኩፍኝ በሽታ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ20 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ በፈረንጆች 2023 ከ10 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኩፍኝ መያዛቸውን አስታውሶ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ከ20 በመቶ በላይ መጨመሩን…

የአሜሪካ እና የቻይና ፕሬዚዳንቶች ፔሩ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና አቻቸው ሺ ዢንፒንግ በእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚክ ትብብር ጉባዔ ለመሳተፍ ፔሩ ሊማ ገቡ፡፡ ፕሬዚዳንቶቹ ሊማ ሲደርሱ በፔሩ አቻቸው ዲና ቦሉአርቴ  ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል፡፡ በስልጣን ዘመን…