Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የጦር ካቢኔያቸውን በተኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገሪቱን ጦር ካቢኔ መበተናቸው ተሰምቷል፡፡ ውሳኔው የእስራኤል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የጦር ካቢኔው መበተን ውሳኔ የእስራኤል…

እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ዕርዳታ እንዲገባ በሚል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን ገታች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ዋና መንገድ ተጨማሪ ዕርዳታ እንዲገባ ወደፊት ገደቡ መነሳቱ እስከሚገለጽ ድረስ በየቀኑ ለተወሰኑ ሠዓታት ወታደራዊ እንቅስቃሴውን መግታቱን አስታወቀ፡፡   እንደ ጦሩ ገለጻ÷ ከኬረም- ሻሎም ማቋረጫ ወደ…

ህንድ በእሳት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 45 ዜጎቿን አስከሬን ከኩዌት ወሰደች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህንድ አየር ኃይል በኩዌት ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የ45 ዜጎች አስከሬን ወደ ሀገራቸው አምጥቷል። የእሳት አደጋው የተከሰተው ከትናንት በስቲያ በኩዌት በማንጋፍ ከተማ 176 ህንዳውያን ሰራተኞች በሚኖሩበት ሕንፃ ላይ ነው።…

የቡድን 7 ሀገራት የሩሲያ ንብረቶችን በዋስትና በመያዝ 50 ቢሊየን ዶላር ብድር ለዩክሬን ፈቀዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 7 ሀገራት የተያዙ የሩሲያ ንብረቶችን በዋስትና በመጠቀም 50 ቢሊየን ዶላር ብድር ለዩክሬን እንዲሰጥ ተስማምተዋል፡፡ የቡድን 7 አባል ሀገራት መሪዎች በሐማስ እና እስራኤል እንዲሁም በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ላይ በጣልያን እየመከሩ ነው፡፡…

በኮንጎ በደረሰ የጀልባ አደጋ ከ80 በላይ መንገደኞች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ አቅራቢያ በሚገኝ ወንዝ ላይ 270 በላይ ተሳፋሪዎችን ጭና የነበረች ጀልባ ተገልብጣ ከ80 በላይ መንገደኞች ህይወት ማለፉን ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ትሺሴኬዲ አስታውቀዋል።   በሀገሪቱ በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ…

በኩዌት የቤት ሰራተኞች በሚኖሩበት ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ41 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት ማንጋፍ ግዛት በመኖሪያ ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ የ41 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ አደጋው የቤት ውስጥ ሰራተኛ የሆኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች በብዛት በሚኖሩበት ሕንጻ ላይ መከሰቱ ነው የተገለጸው፡፡ በእሳት አደጋው ቢያንስ…

የኮንጎ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በይፋ ሥራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁዲት ሱሚንዋ ቱሉካ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጽመው በይፋ ሥራ ጀምረዋል፡፡ ከቤልጂየም ዩኒቨርሲቲ ሊብሬ ዴ ብሬክስልስ በአፕላይድ ኢኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ቱሉካ፥ ከፈረንጆቹ 2020…

እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥ ተገደለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ላይ ጥቃት የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥ ታሌብ አብደላህ ተገደለ፡፡ ታሌብ አብደላህ የእስራኤል ጦር ትናንት ምሽት በደቡባዊ ሊባኖስ ጆዩያ በተሰኘ አካባቢ በፈጸመው የአየር ጥቃት ነው የተገደለው፡፡ በቅጽል…

የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 9 ሰዎችን ያሳፈረ አውሮፕላን መከስከሱ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍሮ ትናንት ተሰውሯል የተባለው አውሮፕላን መከስከሱ ተረጋገጠ፡፡ በደረሰው የመከስከስ አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎች ሕይወታቸው ማለፉን የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ማሳወቃቸውን ቢቢሲ…

አፍሪካ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርም እንዲፋጠን ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርም እንዲፋጠን ጠይቀዋል፡፡ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ሪፎርምን በማስመልከት የአፍሪካ ህብረት ከ10 ሀገራት የተውጣጣው የሚኒስትሮች ኮሚቴ 11ኛው ጉባኤ በአልጀርስ…