Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
የማው ማው ንቅናቄ ከእንግሊዝ መንግስት የ2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬኒያው ማው ማው ንቅናቄ እንግሊዝ በቅኝ ግዛት ለፈፀመችው ግፍ የ2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ካሳ መጠየቁ ተገለፀ፡፡
ንቅናቄው በፈረንጆቹ 1952 የተመሰረተ ሲሆን ኬንያ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት በ1960 ነፃ እንድትወጣ ትግል ሲያደርግ የነበረ ነው፡፡…
ተመድ ለጋዛ የሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለጋዛ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ሀገራት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
አሜሪካ ፣ ብሪታንያን፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፊንላንድ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ኔዘርላንድስ ለጋዛ ሲያደርጉት የነበረውን…
አሜሪካ ለቱርክና ግሪክ የጦር ጄቶች እንዲሸጡ ፈቀደች
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጆ ባይደን አስተዳደር የጦር ጄቶች ለቱርክ እና ለግሪክ እንዲሸጡ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቋል፡፡
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትና የመከላከያ ደህንነት ትብብር ኤጀንሲ እንደገለፁት፤ በስምምነቱ መሰረት ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ለቱርክ እንዲሁም…
ሂዝቦላህ በ9 የእስራኤል የጦር ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ በድንበር አቅራቢያ በሚገኙ 9 የእስራኤል የጦር ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታውቋል፡፡
በጥቃቱ ሚሳኤሎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ጥቅም ላይ ማዋሉንም ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የእስራኤል ጦር…
ሲአይኤ እና ሞሳድ ከኳታር ባለስልጣናት ጋር በእርቅና እስረኞችን በለመለዋወጥ ጉዳይ ሊመክሩ ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላ ኤጀንሲ (ሲአይኤ) ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ እና የእስራኤል የሞሳድ ኃላፊ ዴቪድ ባርኔያ በጋዛ የሚገኙ ምርኮኞችን ለማስፈታት እና ጦርነቱን ለማስቆም የሚያስችል ሁለተኛ ስምምነት ለማድረግ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ…
በቀይ ባህር ላይ የሚካሄደው የንግድ እንቅስቃሴ 42 በመቶ ቀንሷል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁቲ አማፂያን በሚፈፅሙት ጥቃት ምክንያት በቀይ ባህር ላይ የሚካሄደው የንግድ እንቅስቃሴ 42 በመቶ መቀነሱን የተባበሩት መንግሰታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ፡፡
የንግድ እንቅስቃሴው መቀነስ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በችግር ውስጥ…
በማሊ በወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሊ በወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ የመደርመስ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራብ ኩሊኮሮ አካባቢ በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ ነው የተከሰተው፡፡
በአካባቢው የወርቅ ማዕድን አውጪዎች ሃላፊ…
ኢራንና ቱርክ የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት እንዲቆም ለማድረግ በጋራ እንደሚሰሩ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራንና ቱርክ የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ወደ ቀጣናው እንዳይስፋፋ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከቱርኩ አቻቸው ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነትን…
65 ዩክሬናውያን የጦር እስረኞችን ይዟል የተባለ አውሮፕላን መከስከሱ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 65 ዩክሬናውያን የጦር እስረኞችን ይዟል የተባለ የሩሲያ አውሮፕላን መከስከሱ ተሰምቷል፡፡
ንብረትነቱ የሩሲያ የሆነው ወታደራዊ አውሮፕላን ሀገሪቱ ከዩክሬን በምትዋሰንበት ደቡባዊ ቤልጎሮድ ግዛት ነው የተከሰከሰው፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር…
ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የመገናኘት የተስፋ ምልክት ሀውልትን ማፍረሷ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሁለቱ ኮሪያዎች በሰላም መገናኘት እንደማይችሉ ከተናገሩ ከቀናት በኋላ የሀገራቱ የመገናኘት የተስፋ ምልክት የሆነው ሀውልት መፍረሱ ተሰምቷል፡፡
በኮሪያ ባሕረ ሰላጤ ያለው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ…