Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አ.ማ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ከጅቡቲ አዲስ አበባ ማጓጓዝ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር በኩል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጓጓዙ 63 የጭነት ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።   አክሲዮን ማህበሩ ከዚህ ቀደም መደበኛ ተሽከርካሪዎችንና የቤት አውቶሞቢሎችን ብቻ ሲያጓጉዝ…

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ ገባ። ልዑኩ ቤጂንግ ሲደርስ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች እና በቻይና…

ጃፓን “ኔቶ”ን የመቀላቀል ዕቅድ የላትም – ፉሚዮ ኪሺዳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት “ኔቶ”ን የመቀላቀል ዕቅድ እንደሌላት የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ አስታወቁ፡፡ ፉሚዮ ጃፓን በማናቸውም መንገዶች አሜሪካ መራሹን የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት አትቀላቀልም ሲሉ አቋማቸውን…

የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንተና እና ትንበያ ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 64ኛው የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንተና እና ትንበያ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ፎረሙን የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የአየር ትንበያ ማዕከል ጋር በመተባበር…

ከ209 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ209 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ከግንቦት 4 እስከ ግንቦት 10 ቀን  2015 ዓ.ም ባደረገው  ክትትል ነው 209 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ…

የሶማሌ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ውይይት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ውይይት መካሄድ ጀምሯል፡፡ ውይይቱ "የመንግሥት ቅቡልነት ምንነት፣ ማረጋገጫ መንገዶችና የብልፅግና አቅጣጫዎች "በሚል መሪ-ቃል ነው የሚካሄደው፡፡ #Ethiopia…

በዘመናዊው የአውሮፓ እግር ኳስ የዘረኝነት ጥቃት አሁንም እልባት አላገኘም

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘመናዊው የአውሮፓ እግር ኳስ በጥቁር ተጫዋቾች ላይ የሚደርሰው የዘረኝነት ጥቃት እስካሁን አልባት አላገኘም፡፡  በአውሮፓ እግርኳስ በተለያዩ ጊዜያት በጥቁር ተጫዋቾች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት በእግርኳስ ህግጋቶችን አልፎ ዛሬም ድረስ…

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀረጥ ነጻ የሚሸጡ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው – አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ማዕከል ከቀረጥ ነጻ የሚሸጡ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች አበረታች ውጤት እያመጡ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ፡፡ አቶ መላኩ አለበል ከአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ጋር በአየር…

አዲስ አበባና ዴንቨር በጋራ የሚሰሩባቸውን ዘርፎች ወደ ተግባር መለወጥ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ እና ዴንቨር ከተሞች በጋራ የሚሰሩባቸውን ዘርፎች ወደ ተግባር መለወጥ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዴንቨር በነበራቸው ቆይታ ከከተማው ከንቲባ ማይክል ሃንኮክ ጋር በጋራ ለመሥራት የተለዩ ዘርፎችን…

ቤልጄም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ቤልጄም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽንና በአቅም ግንባታ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገለፀች። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ( ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከቤልጄም አምባሰደር ስቴፈን ቲጅስ ጋር ተወያይተዋል።…