Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት እና የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስን ያገናኘው የሊጉ የመጨረሻ ጨዋት 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡…

የአፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የክረምት ወራት ሥራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የክረምት ወራት ሥራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በአፋር ክልል የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ በግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ እና የክልሉ ከፍተኛ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሐምሌ 10 ቀን በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ በመትከል ታሪክ እንዲሰራ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፊታችን ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ በመትከል ታሪክ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት…

የጃፓን ባለሐብቶች መዋዕለ-ንዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን ባለሐብቶች እና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የጃፓን ኤምባሲ “ኢንስፓየር አፍሪካ” ከተሰኘ ማኅበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች…

ሩሲያ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት ሩስያ ትብብርና ድጋፍ እንደምታደርግ በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪን ተናገሩ። የአየር ሁኔታ መለወጥ የውሃ ሃብትን በመቀነስ፣ በግብርና ምርት ላይ ጫና በማሳደርና…

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ለመቀነስ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል- አቶ ደመቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ለመቀነስና ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡ አቶ ደመቀ÷ የዓለም አቀፉ የአየር…

በደቡብ እና ሐረሪ ክልሎች የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ እና ሐረሪ ክልሎች የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ ተጀምሯል፡፡ በደቡብ ክልል ሕዝባዊ ንቅናቄውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን የቡኢ አዳሪ ት/ ቤት…

አቶ መስፍን ጣሰው የኤርባስ A350 አውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የተቋሙ አመራሮች በእንግሊዝ የሚገኘውን የኤርባስ A350 አውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እንግሊዝ በረራየጀመረበትን 50ኛ…

ፋሲል ከነማ ተጫዋቾች እንዳያዘዋውር ታገደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከስምንት ቀናት በኋላ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ተጫዋች እንዳያስፈርሙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ አሳልፏል።   ክለቡ የታገደው ከቀድሞ አሰልጣኙ ኃይሉ ነጋሽ የደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ…

ተቋማትና ድርጅቶች ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደቀጠሉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋማትና ድርጅቶች ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደቀጠሉ ነው። በ16ኛው ዙር የተለያዩ ተቋማት ከ76 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለትውልድ ድጋፍ ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል። …