Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ፓሊሳዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ፋሃድ ኦባይዱላህ አል-ሁመይዳኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡   በውይይታቸውም የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል…

እስካሁን በአማራ እና አፋር ክልሎች 209 ትምህርት ቤቶች ወደ ሥራ አልተመለሱም

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግጭቱ ምክንያት በደረሰባቸው ውድመትና ከፊል ጉዳት እስካሁን በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ 209 የትምህርት ተቋማት ወደ አገልግሎት አለመመለሳቸውን የየክልሎቹ ትምህርት ቢሮዎች አስታወቁ፡፡ በክልሎቹ ከሦስተኛው ዙር ግጭት በፊት በ4 ሺህ 365…

በየዘርፉ ያሉ ልሂቃን ለብሔራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዘርፉ ያሉ ልሂቃን በአገር ጉዳይ ላይ ተቀራርበው በመሥራት ለብሔራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የሰላም ሚኒስቴር በሀገራዊ ምክክርና ዘላቂ የሰላም ግንባታ…

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት ከፍተኛ ልዑክ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ አቅንቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ 9 አባላት ያሉት ልዑክ ለሥራ ጉብኝት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ አቅንቷል፡፡   ልዑኩ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሊሰራቸው ባቀዳቸው ትላልቅ የልማት ስራዎች…

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 5 ወራት ከ744 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 5 ወራት ከ744 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ። የኦሮሚያ ስራ እድል ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ በጅማ ከተማ የመቶ ቀናት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የስራ ፈጣሪነት ንቅናቄ ማካሄድ ጀምሯል። የኦሮሚያ ስራ…

አሜሪካ ዕገዳ ለጣለችባቸው የቻይና ገቢ ምርቶች ፍቃድ ልትሠጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ስትል ዕገዳ ለጣለችባቸው የቻይና ምርቶች ዝርዝር ፍቃድ ልትሠጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የገቢ ንግድ ዕግዱ የሚነሳው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር በቅርበት ለመሥራት ፍላጎት ማሳየታቸውን…

ማረሚያ ቤቶችን ከማረሚያ ማዕከልነታቸው ባለፈ የስልጠና እና የምርታማነት ስፍራ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – አቶ ዳመነ ዳሮታ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2015 (ኤፍ. ቢ. ሲ.) ማረሚያ ቤቶችን ከማረሚያ ማዕከልነታቸው ባለፈ የስልጠና እና የምርታማነት ስፍራ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አቶ ዳመነ ዳሮታ ተናገሩ። በወጣት ጥፋተኝነት፣ በአማራጭ ቅጣቶች እና…

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በበጋ ስንዴ ምርት ከ10 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለማምረት እየሰራሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጋ ስንዴ ምርት ከ10 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለማምረት እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ሀይለማሪያም ከፍያለው እንደተናገሩት በክልል ደረጃ ከ250 ሺህ በላይ መሬት በስንዴ ዘር በመሸፈን ለውጭ ገበያ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአሜሪካ ጉብኝት በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአሜሪካ ጉብኝት በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያጎለብት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።   የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ…

የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ ታኅሣሥ 18 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ ለ6ኛ ጊዜ ታኅሣሥ 18 እንደሚካሄድ ተገለጸ። ኦዳ አዋርድ የኦሮሚኛ ቋንቋ የጥበብ ስራዎችንና ባለሙያዎችን አወዳድሮ እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፥ በዘንድሮው የኦዳ አዋርድ ሽልማት ላይ አስተባባሪዎቹ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡…