Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎ እና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ፡፡ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ የሰላም ሂደቱን ለማጠናከር…

ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፏል። የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ በአካሄደው ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያው ያለውን አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ…

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ሥር በሚገኙ ሥድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ፡፡ በስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ)…

በጋራ የተመዘገቡ ድሎችን ለማፅናት የሚያስችል ምክክር ማካሄዳቸውን የአማራ እና የኦሮሚያ ብልፅግና ፅህፈት ቤቶች ሀላፊዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋራ የተመዘገቡ ድሎችን ለማፅናት እና ፈተናዎችን በወንድማማችነት ለመሻገር የሚያስችል ምክክር ማካሄዳቸውን የአማራ እና ኦሮሚያ ብልፅግና ፅህፈት ቤቶች ሀላፊዎች ተናገሩ። ለዘላቂ ሠላም እና ሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል በሁለቱ ክልሎች…

ከ300 ለሚበልጡ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ከ300 በላይ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና መስጠቱን ገለጸ። የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የ2022 የሥራ ዘመን በልብ ማዕከል ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን…

11 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በሀሰተኛ ሰነድ ሸጠው ገንዘቡን በመከፋፈል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 11 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በሀሰተኛ ሰነድ ለልማት ተነሺ በሚል ሸጠው ገንዘቡን ሸጠው ገንዘቡን ተከፋፍለዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ፡፡ ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ…

ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በትኩረት እየተሰራ ነው – የአማራ ክልል

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የገበያ ያለመረጋጋት እንዳይከሰት ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል የንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ የንግድ…

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ታዳጊ ዳግማዊ የኳስ ችሎታውን እንዲያዳብር ድጋፍ ልናደርግለት ይገባል አሉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ታዳጊ ዳግማዊ ቴዎድሮስ የኳስ ችሎታውን እንዲያዳብር ድጋፍ ልናደርግለት ይገባል አሉ፡፡ ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ የ12 ዓመቱ ታዳጊ ዳግማዊ ቴዎድሮስን ከአባቱ ቴዎድሮስ ባጫ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው…

እስራኤል በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ላይ ማሻሻያ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ለውጭ ሃይሎች ተጽዕኖ ሳትንበረከክ ብሄራዊ ጥቅሟን ታስከብራለች ሲሉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ተናገሩ፡፡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት ኔታንያሁ በቅርቡ አዲስ መንግስት መስርተዋል፡፡ ጠቅላይ…

ኢትዮ-ቴሌኮምና ጌትፋክት ኢትዮጵያ “ብሩህ ትወልድ” የተባለ የትምህርት ፕሮግራም በጋራ ለማካሄድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮምና ጌትፋክት ኢትዮጵያ "ብሩህ ትወልድ" የተባለ የትምህርት ፕሮግራም በጋራ ለማካሄድ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ የኢትዮ ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚህ ወቅት ÷ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚሰራው ስራ…