Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ከ20 ላይ ይካሄዳል፡፡ በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው እና ሁለተኛ ቀኑን በያዘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና÷ ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር…

ፕሬዚዳንት ባይደን ኢራን የቀጠናው ስጋት በማትሆንበት ሁኔታ ላይ ከባህረ ሰላጤ ሀገራት ጋር ዛሬ ይመክራሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢራን የቀጠናው ስጋት በማትሆንበት እና ተፅዕኖዋን መግታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባህረ ሰላጤ ሀገራት ጋር ዛሬ ይመክራሉ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የአራት ቀናት የአካባቢው አገራት ጉዞ ማሳረጊያ ባደረጉት በዚህ ጉባኤ የባህረ ሰላጤው…

ልጆችና ችግኝ አንድ ናቸው ሁለቱም እንክብካቤን ይሻሉ – ዶክተር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ልጆችና ችግኝ አንድ ናቸው ሁለቱም እንክብካቤን ይሻሉ ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ ተገኝተው ችግኝ…

የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት – ዶክተር ይናገር ደሴ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አሳሰቡ፡፡ 10 ሺህ ያህል ባለአክሲዮኖች ያሉት አሐዱ ባንክ ዛሬ በይፋ ሥራውን ጀምሯል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ  ዶክትር ይናገር ደሴ…

በ2014 በጀት ዓመት በአፋር ክልል ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ መሀመድ ሀሰን እንደገለጹት÷ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡…

በትግራይ ክልል በሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እህል ማቅረብ በመቻሉ  ሊያጋጥም የነበረ የረሃብ አደጋ መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በትግራይ ክልል በሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እህል ማቅረብ በመቻሉ ሊያጋጥም ይችል የነበረን የረሃብ አደጋ መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለፀ። የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮው የሰሜን ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አድሪያን ቫን ደር…

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 493 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 493 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ መንግሥት ሥራ…

አቶ ርስቱ ይርዳ እና አቶ አህመድ ሽዴ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አካል በሆነው በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ ችግኝ ተክለዋል። የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ…

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያየ ሙያ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያየ ሙያ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል፡፡ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በበማታው የትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 974 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ወቅት…

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በወዳጅነት አደባባይ አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ተለያዩ ከፍኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የዩኒቨርሲቲው…