Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሳምንት መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በወዳጅነት አደባባይ መከበር ጀምሯል። በዓሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከፈቱት ሲሆን የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።…

ሰበታ ከተማ አዳማ ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና የራቀበትን ውጤት አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰበታ ከተማ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። ሰበታ ከተማ በመጀመሪያው አጋማሽ 35ኛው ደቂቃ ላይ ኦሴ ማወሌ ባስቆጣራት ብቸኛ ግብ ነው ማሸነፍ መቻሉን ከሱፐር ስፖርት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በዚህም…

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ከኮቪድ 19 በኋላ ኢኮኖሚው እንዲያገግም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከፈረንሳይ የግምጃ ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል ኢማኑኤል ሞውሊን ጋር ከኮቪድ 19 በኋላ ኢኮኖሚው እንዲያገግም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ባለፉት አስርት ዓመታት የተገኙ…

ከ19ሺህ በላይ አረጋዊያን የሴፍቲኔት ተጠቃሚ መደረጋቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ከ19ሺህ በላይ አረጋዊያን በየወሩ የሴፍቲኔት ቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ፡፡ ቢሮው "ወቅታዊና…

ግብፅ የጋዛ ሰርጥን መልሶ ለመገንባት 500 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብፅ በፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ እና እስራኤል መካከል እየተካሄደ በሚገኘው ግጭት ጉዳት የደረሰበትን የጋዛ ሰርጥ መልሶ ለመገንባት 500 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች። የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ድጋፉ ሰሞኑን እየተካሄ…

በ250 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባውን መናሀሪያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡሌ ሆራ ከተማ በ250 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባውን መናሀሪያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ በምክትል ፕሬዚደንት ማዕረግ የኦሮሚያ ማህበራዊ ጉዳይ ክላስተር አስተባባሪ በአቶ አዲሱ አረጋ የተመራው ልዑክ ቡድን በከተማው…

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነችና የቀድሞው ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለበከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከቀድሞው ምክትል ከንቲባ እና የማዕድን እና ነዳጅ ሚንስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን የ1 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ታላቁ ቤተ መጽሀፍት ግንባታና የማዘጋጃ ቤት እድሳትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።…

የፖስታ አገልግሎት የዲጂታል ፍኖተ ካርታ ወደ ትግበራ ሊገባ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የጀርመን መንግስት ድጋፍ ያደረገለት የፖስታ አገልግሎት የዲጂታል ፍኖተ ካርታ ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑ ተገለጸ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎትና የጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮችና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ፖስታ…