Fana: At a Speed of Life!

በለውጡ ማግስት ከተሞች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል – ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት የዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በመድረኩ እንደተናገሩት…

የዓለም ጤና ድርጅት እና ካናዳ በኢትዮጵያ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለሟሟላት የሚያስችል ድጋፍ ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የጤና ድርጅት በኢትዮጵያና የካናዳ መንግስት ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለሟሟላት የሚያስችል ድጋፍ ይፋ አደረጉ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ አቅምን ለማጠናከር ያለመው ይህ ድጋፍ 9 ነጥብ 9 ሚሊየን…

በአዲስ አበባ 10 ሺህ 500 የላዳ ታክሲዎች በአዳዲስ ታክሲዎች ሊተኩ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 ሺህ 500 ሰማያዊ በነጭ የላዳ ታክሲዎችን በአዳዲስ ታክሲዎች ለመተካት ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስአበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ከሃምሳ ዓመታት በላይ አገልግሎት የሰጡትን እነዚህን ተሽከርካሪዎች በዘመናዊ ታክሲዎች መተካት…

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ስራ የተመደበን ገንዘብ ያለአግባብ ጥቅም ላይ ያዋሉ ግለሰቦች ተቀጡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ተግባር የተመደበን ገንዘብ ያለአግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረጉ ሶስት የስራ ሀላፊዎች እስከ ስድስት አመት በሚደርስ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ። የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት…

ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ በማለፍ ጠንካራ ሀገር ትሆናለች – አምባሳደር ፍፁም አረጋ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንኛውም ሀገር ኢትዮጵያ ከህወሓት የጥፋ ቡድን የገጠማትን አይነት ክህደት ቢገጥመው ምላሹ ምን እንደሆነ ይታወቃል አሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ፡፡ አምባሳደሩ ማንኛውም ሀገር በመከላከያ ላይ የሚፈፀምን ጥቃት አይታገስም ሲሉ…

በጋምቤላ ከተማ የአድዋ ፓርክ ተሰየመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክትር ሂሩት ካሳው እና የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት በጋምቤላ ከተማ የአድዋ ፓርክ ተሰይሟል፡፡ ፓርኩ የተሰየመው 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በጋምቤላ ክልል በድምቀት በተከበረበት ወቅት…

ጃፓን በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 265 ሚሊየን ብር ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ድጋፍ ይፋ አደረገች፡፡ ድጋፉ በአብዛኛው ሴቶችና ህጻናትን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም የጃፓን ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ አጠቃላይ ድጋፉ…

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት ኮርፖሬሽኖች ከታክስ በፊት ብር 257 ሚሊየን አተረፉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር ከሚገኙ 21 የልማት ድርጅቶች መካከል በኮንስትራክሽ ዘርፍ የተሰማሩት ሁለት ድርጅቶች 257 ሚሊየን ብር አተረፉ። የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ…

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፒ ኤስ ጂ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተጀምረዋል፡፡ በምሽቱ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ ፒ ኤስ ጂ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በካምፕ ኑ ባርሴሎና ከፒ ኤስ ጂ ባደረጉት ጨዋታ የፈረንሳዩ ክለብ በሰፊ የጎል ልዩነት…

በሐዋሳ በተለምዶ ቤተሰብ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በመሀል ከተማ ክፍለከተማ በአዲስ አበባ ቀበሌ በተለምዶ ቤተሰብ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡ የሐዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ የአደጋው…