Fana: At a Speed of Life!

ከባህርዳር ከተማ የሚወጣው ፍሳሽ ቆሻሻ ከ70 እስከ 80 በመቶው በቀጥታ ወደ ጣና ሐይቅ ይገባል – ጥናት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍቢሲ) ከባህርዳር ከተማ የሚወጣው ፍሳሽ ቆሻሻ ከ70 እስከ 80 በመቶው በቀጥታ ወደ ጣና ሐይቅ እንደሚገባ በአንድ ጥናት ተመላክቷል፡፡ በአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስተባባሪነት ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ወሰን "የጣና ሐይቅ ዳርቻ…

አምባሳደር ነብያት የህግ ማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁን ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ በስኬት መጠናቁን ገለጹ፡፡ አምባሳደር ነብያት ከአልጀሪያው ኤል ቻብ ጋዜጣ ጋር በትግራይ ክልል ከተወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ሃገራዊ ጉዳዮች…

ፓርቲዎች የተሻለ ሀሳብ በማቅረብ ከዴሞክራሲ እሴቶች ካፈነገጡ አካሄዶች የታረመ ተግባር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሻለ ሀሳባቸውን በምርጫ በማቅረብ ከዴሞክራሲ እሴቶች ካፈነገጡ አካሄዶች የታረመ ተግባር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ የህግ ምሁራን ተናገሩ፡፡ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የህግ ምሁራን የፖለቲካ ፓርቲዎች…

የደራሲና ተዋናይ ተ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደራሲና ተዋናይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ የተለያዩ መፅሃፍትን የደረሱ ሲሆን በተለያዩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይም በተዋናይነት ተሳትፈዋል። ዛሬ…

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሠራዊት ልጆች የመማሪያ ቁሳቁሶችን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለመከላከያ ሰራዊት ልጆች ደብተር፣ እስክርቢቶ እና እርሳሶችን ማበርከቱ ተገልጿል፡፡ የስፖርት ክለቡ ለሠራዊቱ ልጆች መማሪያ የሚሆን 50 ሺህ ደብተሮችን፣ 5 ሺህ እስክርቢቶና 5 ሺህ እርሳሶችን አበርክቷል፡፡…

ሰዎችን በማገት 30 ሚሊየን ብር ሲጠይቁ እና ከባድ ውንብድና ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ 5 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮማንደርና ደህንነት ነን እያሉ ሰዎችን በማገት 30 ሚሊየን ብር ሲጠይቁ እና ከባድ ውንብድና ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ 5 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዛሬ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የታዩት ተጠርጣሪዎች ያሬድ ኦሊቃ እና ፍቃዱ እዮኤልን ጨምሮ አምስት…

እነጃዋር መሀመድ በአቅራቢያችን ችሎት ጉዳያችን ይታይልን ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህገመንግስትና የፀረ ሽብር ወንጀሎች ጉዳይ ችሎት የእነ ጃዋር መሀመድን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል፡፡ ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን…

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ በተደረገላቸው ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ለሰባት ቀናት…

በትግራይ ከጁንታው ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦነግ ሸኔ አባል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ22 አመት ወጣት ሲሆን ፈይሳ ተካ ይባላል፡፡ ትውልድና እድገቱ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረት ከተማ ነው፡፡ ትምህርቱን ከስምንተኛ ክፍል አቋርጦ ሀገራችንን ነጻ እናውጣ እያለ በሚሰብከው ታደሰ ጆንሴ በሚባል ሰው አማካኝነት…

የብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፅሐፍት ኤጀንሲ አቋርጦ የነበረውን አገልግሎት ታህሳስ 12 ቀን ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፅሐፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር) በኮቪድ- 19 ምክንያት አቋርጦት የነበረውን አገልግሎት ከታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መመሪያን ጠብቆ ቤተ መፅሐፍቱን…