Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ በአውሮፕላን ማረፊያዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታንያ በአውሮፕላን ማረፊያዎች ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሯ ተነግሯል። በዛሬው እለት ከለንደን ሂትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሆንግ ኮንግ በረራ ያደረጉ መንገደኞች ፈጣን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተነግሯል።…

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሲዳማ ክልል የማዕድን ቁፋሮ የሚካሄድባቸውን ስፍራዎች ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ የተመራ ልዑክ በሲዳማ ክልል የማዕድን ቁፋሮ የሚካሄድባቸውን ስፍራዎች በዛሬው እለት ጎብኝቷል። ኢንጂነር ታከለ በጉብኝታቸው ከሀዋሳ 180 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የገናሌ ወንዝ ገባር በሆነው በሎጊታ…

አዲስ ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተዘረጋን የኤሌክትሪክ መስመር የሰረቁ ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተዘረጋን የኤሌክትሪክ መስመር የሰረቁ ሦስት ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት…

በሶማሌ ክልል ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለሙ ከፍተኛ ማሽነሪዎች ለአርሶ አደሩና በግብርና ለተሰማሩ ወጣቶች ሊከፋፈሉ  ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለሙ ከፍተኛ ማሽነሪዎች ለአርሶ አደሩና በማህበር ተደራጅተው በግብርና ለተሰማሩ ወጣቶች እንደሚከፋፈሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ አስታወቁ። ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን…

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታጣቂዎች 900 እስረኞችን አስለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቤኒ ከተማ ታጣቂዎች 900 እስረኞችን ማስለቀቃቸው ተገለፀ። ከካንግባዩ እስር ቤት ካመለጡት 900 እስረኞች መካከል የታጣቂ ቡድን አባላት እንደሚገኙበት ቢቢሲ የከተማዋን ከንቲባ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።…

ዓለም አቀፉ የትምህርት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በዓለም አቀፉ የትምህርት ጉባኤ ላይ በበይነ መረብ እየተሳተፉ ነው፡፡ ጉባኤው በጋና፣ የኖርዌይ፣ እንግሊዝ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) በ ጋራ…