Fana: At a Speed of Life!

23 ሺህ ግራም ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናትናው ዕለት 46 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው 23 ሺህ ግራም ወርቅ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። 23 ሺህ ግራም ወርቁ ናይጄሪያ ዜግነት ባለው ግለሰብ ከሀገር ሊወጣ ሲል በቦሌ አየር መንገድ መያዙን ነው ሚኒስቴሩ…

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ከ16 አመት በኋላ ተሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ትናንት ማታ በዑጋንዳዊው አትሌት ቼፕቴጌ ተሻሽሏል፡፡ ጆሹዋ ቼፕቴጌ ትናንት ምሽት በሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የ5 ሺህ ሜትሩን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች አሻሽሎታል፡፡…

አሜሪካ በኢራን ላይ የተጣለው የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲራዘም ያቀረበችው የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አሜሪካ በኢራን ላይ የተጣለው የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲራዘም ያቀረበችውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አደረገ፡፡ ምክር ቤቱ ሌሊቱን ባደረገው ስብሰባ ዋሽንግተን በቴህራን ላይ ላለፉት 13 አመታት…

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ጋር ተወያይተዋል። በዚህ ወቅትም የከተማ አስተዳደሩ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች…

የኦሮሚያ፣ የአማራ ክልሎችና ገቢዎች ሚኒስቴር በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ፣ የአማራ ክልሎችና ገቢዎች ሚኒስቴር በአፋር ክልል ጎርፍ ጉዳት ላደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረጉ። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እና የኦሮሚያ ክልል ልዑካን ቡድን…

በቻምፒየንስ ሊጉ ሙኒክ ባርሴሎናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፎታል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በተደረገ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ከባድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ በሊዝበን በተደረገው ጨዋታ የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ባርሴሎናን 8 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፎታል፡፡ በጨዋታው ቶማስ ሙለር እና ተቀይሮ…

በ24 ሰዓታት 1ሺህ 38 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 17 ሺህ 323 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 38 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 27 ሺህ…

በአዲስ አበባ ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እስካሁን ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ እስካሁን ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ላይ የኮሮና ቫይረስን ለመለየት ናሙና መወሰዱን ጤና ቢሮው አስታውቋል። ቢሮው…

ጠ/ሚ ዐቢይ በሸገርን ማስዋብ ስራ ላይ ለተሰማሩ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሸገርን ማስዋብ ስራ ላይ ለተሰማሩ አካላት ምስጋና አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ የከተማችን ገፅታ የላቀ ለውጥ እንዲያሳይ ላደረጉ እና ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውን እና ጉልበታቸውን…