አፈ- ጉባዔዋ በጠሩት የምክር ቤቱ መደበኛ ሰብሰባ ዋዜማ የመልቀቂያ ውሳኔ መስጠታቸው ተገቢነት የለውም- ፌዴሬሽን ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አፈ-ጉባኤዋ በጠሩት የምክር ቤቱ መደበኛ ሰብሰባ ዋዜማ የመልቀቂያ ውሳኔ መስጠታቸው ተገቢነት የሌለውና እንደ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካይ ኃላፊነት ትክክለኛ ያልሆነ ውሳኔ እንደሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ።
አፈጉባዔዋ ዛሬ ልዩነት አለኝ ብለው…
ህብረተሰቡ በኮቪድ19 ስጋት በጤና ተቋማት የሚያገኘውን የህክምና አገልግሎት ማቋረጥ የለበትም – ዶክተር ሊያ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ስጋት ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የሚያገኘውን የህክምና አገልግሎት ማቋረጥ እንደሌለበት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
ዶክተር ሊያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የኮቪድ19 ወረርሺኝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ…
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ማውሪን አቼንግ ጋር ተወያዩ።
አቶ ገዱ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ ተጠናክሮ…
የኮሮና ቫይረስ ወደ ስደተኞች መጠለያዎች እንዳይገባ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በድንበር አካባቢ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያዎች እንዳይገባ ጠንካራ የቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የኢትዮጵያ የስደትና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ገለጸ።
ኢትዮጵያ መጠለያ በመስጠት እያኖረቻቸው…
ወይዘሮ ኬሪያ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤነታቸው መልቀቃቸውን ገለፁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ገለፁ፡፡
ወይዘሮ ኬሪያ በመቐለ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽን…
በአዲስ አበባ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 625 ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 625 መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ባለፉት 24 ሰአታት በተደረገው ምርመራ በከተማዋ 115 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ጠቅሷል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ…
ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2012 በጀት ዓመት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ፥ በ10 ወራቱ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ…
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቀጠናውን በማስተሳሰር ቀጠናዊ ውህደትን የሚያፋጥን ፕሮጀክት ነው-የኬንያ ፓርላማ የመንግስት ተጠሪ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በዛሬው ዕለት ከኬንያ ፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ከሆኑት አደን ዱዋሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያይተል።
አምባሳደር መለስ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ለአደን ዱዋሌ ገለጻ…
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ ልዩነቶቻችውን በውይይት እንዲፈቱ ሩሲያ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ኢቭጄኒይ ተረክህን ጋር ተወያይተዋል።
አቶ ገዱ አትዮጵያ እና ሩሲያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊና በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዳላቸው በመግለጽ፥ ኢትዮጵያ…