Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪዎች ከቀረጥ ነጻ ሆነው እንደሚገቡ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 624 አይነት የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪዎች ከቀረጥ ነጻ ሆነው የሚገቡ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የግብርና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የግል ባለሀብቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ…

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር ተወያይተዋል። በዚህ ወቅትም ኢንጂነር ታከለ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች…

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን አዋሽ የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 4፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል መቐለ የሚገኘውን አዋሽ የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ዶክተር ደብረፂዮንን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። ስሁል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ ላይ በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት…

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የደረሱ ሰብሎችን የሚሰበስቡ አርሶ አደሮችን አበረታቱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በአርሶ አደሮች ማሳ በመገኘት የደረሱ ሰብሎችን ሰብስበዋል። በዚህም አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ በመሰብሰብ የሚያጋጥመውን የእህል ብክነት ለመከላከል በትጋት…

የኢትዮጵያ እና የህንድ የቴክኖሎጂ ድርጅቶት በቅንጅት መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መሰረቱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ እና የህንድ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች በቅንጅት መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መሰረቱ። ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል። በዚህም…

“የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ” እንዲቋቋም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ”የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ” እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ። የኤጀንሲው መቋቋም በተያዘው ዓመት በሰፊው የተሰራውን የትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦትና የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር ቀጣይነት እንዲኖረው እና…

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 77ኛ መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግስት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ስርዓትን ለመደንገግ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል።…

በዶሃ ፎረም በመሳተፍ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልኡክ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ዓለም አቀፍ ት/ቤትን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ከሚል፣ የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ እንዲሁም የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በፈረንጆቹ ከታህሳስ 14 አስከ 15 በኳታር በሚካሄደው 19ኛው የዶሃ…

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ከአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው። በውይይት መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው፣ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ…