Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ወጣቶች የሚሳተፉበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ወጣቶች የሚሳተፉበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተጀመረ።   ዛሬ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የችግኝ ተከላ እና ደም ልገሳ በማካሄድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በይፋ ጀምሯል ።  …

የሶማሊ ክልል የጎሳ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት መሪዎች የህዳሴ ግድብን እውን ለማድረግ ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የጎሳ መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት መሪዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የጎሳ መሪዎቹ፣ የሀገር ሽማግሌዎቹ እና የሀይማኖት መሪዎቹ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ…

ምርጫ ቦርድ የቀድሞ የኢሕአዴግን ንብረት እንዲያጣሩ ሁለት ኦዲተሮችን ሾመ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ንብረት እንዲያጣሩ ሁለት ኦዲተሮችን ሾመ፡፡   የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ጥር 20 ቀን…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት መሪ ፕላን ረቂቅ ላይ እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት መሪ ፕላን ረቂቅ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የ10 ዓመት እቅዱ እስከ 2022 ዓ.ም ለመከናወን የታቀደ ሲሆን፥ የፖሊሲና ስትራቴጂ ፣ ያለፉት አመታት አፈጻጸምና…

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ41 ሺህ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። አሁን ላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከብሪታንያ በመብለጥ ከ41 ሺህ አልፏል። አሃዙ ከአሜሪካ ቀጥሎ ዓለም ላይ ሁለተኛው…

አሜሪካ እና ኢራቅ በወታደራዊ ጉዳዮች በጋራ መስራት በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ምክክር አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ኢራቅ በወታደራዊ ጉዳዮች በጋራ መስራት በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ምክክር አደረጉ። የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት የአሜሪካ ወታደሮች ወደፊት በኢራቅ በሚኖራቸው ቆይታና በሚሰፍሩበት ሁኔታ እንዲሁም በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ…

በላ ሊጋው ግራናዳ ሲያሸንፍ በኮፓ ኢታሊያ ጁቬንቱስ ለፍጻሜ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ላ ሊጋ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። በሜዳው ጌታፌን ያስተናገደው ግራናዳ ዳኮናም እና ፈርናንዴዝ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል። ቲሞር ለጌታፌ የማስተዛዘኛ ጎሏን አስቆጥሯል። በሌላ ጨዋታ ቫሌንሲያ…

ቢቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በተያያዘ ተናግረውታል ብሎ ላወጣው ዘገባ ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያው የዜና አውታር ቢቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በተያያዘ ብለውታል በሚል ላወጣው ዘገባ ይቅርታ ጠየቀ። ባለፈው ሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ…

ጠ/ሚ ዐቢይ በወሊሶ ከተማ የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎትን በይፋ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በወሊሶ ከተማ ተገኝተው የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎትን በይፋ አስጀመሩ። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር…

አቶ ደመቀ መኮንን ለደብረ ብርሃን ደነባ – ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር – ደነባ የአስፓልት መንገድ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደብረ ብርሃን ደነባ - ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር - ደነባ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ። አጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ 108 ኪሎ…