Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር ከክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችና ኮሚሽነሮች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከክልል የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችና ኮሚሽነሮች ጋር መወያየቱን አስታወቀ። ውይይቱ በገለልተኛ ቡድን አማካሪ ማስፈፀሚያ ማንዋል እና በብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ላይ ያተኮረ መሆኑንም አስታውቋል።…

የደቡብ ክልል ተወላጅ ምሁራን ውይይት በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ተወላጅ ምሁራን ውይይት በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እንዳሉት፥ ውይይቱ ለክልሉ ወቅታዊ ችግሮች የሰከነ ሀሳብና ተሻጋሪ መፍትሄዎችን ለማደራጀት ሚናው የላቀ…

በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ የመከላከል ስራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰኔ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ ከነበረው የአንበጣ መንጋ በተጨማሪ ከሶማሊያ እየገባ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ፣ ጉጂ ፣ ቦረና ዞኖች እንዲሁም በደቡብ ክልል የተለያዩ…

በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ከ5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ባለፉት ስድስት ወራት በ119 የግጭት አደጋዎች ከ5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። 87 ግጭቶች ከቀለበት መንገድ ውጭ ባሉ የመንገድ ሐብቶች ላይ ሲደርሱ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ካቢኔ ተበተነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ካቢኔ ተበተነ። ካቢኔው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የህገ መንግስት ማሻሻያ ማድረግ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ መበተኑ ተገልጿል። ፑቲን ለሃገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ሃገራቸው የህገ…

ጉግል አዲሱን የግላዊነት ፖሊሲ ተግባራዊ የሚያደርግበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎግል የሶስተኛ ወገን አጠቃቀምን የሚገድብ አዲስ የግላዊነት ማስጠበቂያ ፖሊሲ የሚተገበርበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ። ተቋማት በበይነ መረብ ላይ እየጨመረ የመጣውን ጥቃት ተከትሎ የግላዊነት ጥበቃ ደህንነታቸውን እንዲያጠናክሩ የሚያደርግ ግፊት…

የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ቤት ኤኒይ ከተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ህፃናት ያሉባቸውን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ቤት ኤኒይ ከተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ጋር ተፈራረመ። ስምምነቱን በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር…

ባለፉት 3 ዓመታት የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት መሻሻል ታይቶበታል – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 3 ዓመታት የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት መሻሻል ማሳየቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ዓመታት በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት /ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ/ ድጋፍ ሲካሔድ የቆየው የእናቶችና ህጻናት ጤና ማሻሻያ ፕሮጀክት…

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የውሃ ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን እያደረጉት…

በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት 1 ሺህ የሚጠጉ ወደ ሊቢያ መመለሳቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው አዲሱ የፈረንጆች ዓመት 1 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች ወደ ሊቢያ መመለሳቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አስታወቀ። የባህር ላይ ጠባቂዎች የሜዲትራንያንን ባህር ሲያቋርጡ የያዟቸውን ስደተኞች ወደ ሊቢያ መመለሳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።…