Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኤልክላሲኮ – ባርሴሎና የቡድን አንድነቱን ካጣው ሪያል ማድሪድ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር ባርሴሎናን ከሪያል ማድሪድ የሚያገናኘው ኤልክላሲኮ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በካምፕ ኑ ይደረጋል፡፡ በቀደሙት ዓመታት ኤልክላሲኮ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅና ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት መርሐ ግብር ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሁለቱ ቡድኖች የእርስ በርስ ግንኙነት በቀደሙት ዓመታት የነበረውን ከፍተኛ ፉክክሩን እያጣ መጥቷል፡፡ የመጀመሪያው የኤልክላሲኮ ጨዋታ የተደረገው በፈረንጆቹ 1902 ሲሆን ጨዋታውን ባርሴሎና 3 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡…
Read More...

ሃላባ ከተማ የከፍተኛ ሊጉ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሃላባ ከተማ በመለያ ምት ጋሞ ጨንቻን 4 ለ 3 በማሸነፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል። የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የማጠቃለያ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል። በፍፃሜው ሃላባ ከተማን ከጋሞ ጨንቻ ያገናኘው ጨዋታ በመደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ ተጠናቅቋል። የዋንጫውን…

በሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች እንዲለቅ የተፈለገው ምባፔ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን እንዲለቅ በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች ፊርማ እያሰባሰቡ ይገኛሉ፡፡ ምባፔ የሀገሩን ክለብ ፒኤስጂን በመልቀቅ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ፍለጋ ሪያል ማድሪድን ቢቀላቀለም በክለቡ በቆየባቸው ሁለት ዓመታት ይህንን ሕልሙን ማሳካት አልቻለም፡፡ በተቃራኒው…

ከፓሪስ እስከ ቡዳፔስት… 20 ዓመታት የፈጀው ጉዞ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ በመድረኩ ለፍጻሜ ሲያልፍ የዘንድሮው ለ2ኛ ጊዜ ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ለፍጻሜ የደረሰው በ2005/6 የውድድር ዓመት ነበር፡፡ በፈረንጆቹ 2006…

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 አሸንፏል። ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሁለቱንም ግቦች ናትናኤል ዳንኤል አስቆጥሯል። የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 10 ሰዓት ላይ በዚሁ…

ቼልሲ በኖቲንግሃም ፎረስት ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ በኖቲንግሃም ፎረስት 3 ለ 1 ተሸንፏል። አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ የኖቲንግሃም ፎረስትን የማሸነፊያ ግቦች አወንዬ (2) እና ኢጎር ጄሱስ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል፡፡ የቼልሲን ብቸኛ ግብ ደግሞ ብራዚላዊው ጃኦ ፔድሮ…

ኤቨርተን ከማንቼስተር ሲቲ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ ኤቨርተንን ይገጥማል፡፡ የዛሬ ምሽቱን ጨምሮ ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች በእጁ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ከአርሰናል ያለውን የስድስት ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡ በቀጣይ የውድድር አመት የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎን ለማግኘት…