ስፓርት
ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱ ክለቦች ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም አስቀድሞ በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባ ምንጭ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የኢትዮ ኤሌክትሪክን ግቦች በፍቃዱ አስረሳኸኝ ፣ ሀሰን ሁሴን እና አቤል ሀብታሙ ሲያስቆጥሩ፥ አርባ ምንጭ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችውን…
Read More...
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሞሮኮ ከምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆኗል፡፡
ከታንዛኒያ አቻው ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታውን በድሬዳዋ ስታዲየም ያደረገው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡
በድምር ውጤት በታንዛኒያ አቻው 3 ለ 0 በሆነ ውጤት የተሸነፈው…
አትሌት ትዕግስት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ።
የዓለም አትሌቲክስ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ፤ አትሌቶቹ በውድድር ዓመቱ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ባስመዘገቡት ውጤት ነው ለዕጩነት መካተት የቻሉት።
በሴቶች አትሌት ትዕግስት…
አርሰናል ክሪስታል ፓላስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር በሜዳው ኢምሬትስ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው አርሰናል 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ምሽት 11 ሰዓት በተካሄደው በዚህ ጨዋታ አርሰናል መሪነቱን ያጠናከረበትን ብቸኛ ግብ በመጀመሪያ አጋማሽ ኤብሪቼ ኤዜ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎም አርሰናል ነጥቡን ወደ 22…
ቼልሲ በሰንደርላንድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ በሰንደርላንድ 2 ለ1 ተሸንፏል፡፡
በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ጨዋታውን ያደረገው ቼልስ በአሌሃንድሮ ጋርናቾ ግብ ሲመራ ቢቆይም ኢሲዶርና ታልቢ ለሰንደርላንድ ባስቆጠሯቸው ግቦች ተሸንፏል፡፡
በሌላ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ፉልሃምን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ÷…
ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ያሬድ ባዬህ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
ቀደም ብሎ ቀን 6 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምድረ ገነት…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ብራይተንን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ከረጅም ጊዜ በኋላ ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በሊጉ ያሸነፈው ማንቼስተር ዩናይትድ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ይፋለማል።…