ስፓርት
ቶተንሀም ሆትስፐር አንጂ ፖስቴኮግሉን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር የክለቡን አሰልጣኝ አንጂ ፖስቴኮግሉን አሰናብቷል፡፡
አሰልጣኙ በስፐርስ በነበራቸው የሁለት ዓመት ቆይታ የዩሮፓን ሊግ ዋንጫን አሳክተዋል፡፡
በፖስቴኮግሉ የተመራው ቶተንሀም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ደካማ የውድድር ጊዜ አሳልፏል፡፡
በሊጉ ካደረጋቸው 38 ጨዋታዎች በ22ቱ ተሸንፎ፤11 ጨዋታ አሸንፎ በ5 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ መለያየቱ አይዘነጋም፡፡
ውጤቱን ተከትሎም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 38 ነጥብ በመሰብሰብ 17ኛ ደረጃን…
Read More...
ራፊንሀ -የስፔን ላሊጋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጫዋች ራፊንሀ የ2024/25 የውድድር ዓመት የስፔን ላሊጋ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡
ራፊንሀ በውድድር ዘመኑ ለባርሴሎና 36 የላሊጋ ጨዋታዎችን በማድረግ 18 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
እንዲሁም ዘጠኝ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አማቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡
ባርሴሎና…
አርሰናል የጋብሬል ማግሀሌስን ውል አራዘመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ጋብሬል ማግሀሌስን ውል እስከ ፈረንጆቹ 2029 ማራዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ጋብሬል ማግሀሌስ ከአምስት ዓመት በፊት ከሊል ወደ አርሰናል መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡
ማግሀሌስ መድፈኞቹን ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ ለአርሰናል 210 ጫወታዎችን አድርጎ 20…
መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 9 ሠዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቤንጃሚን ኮቴ የመቐለ 70 እንደርታ ማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ረፋድ 3 ሠዓት በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ስሑል…
ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ለሐዋሳ ከተማ አሊ ሱሌማን አራት ግቦችን ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ጎል ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሐዋሳ ከተማው የፊት መስመር ተጫዋች አሊ ሱሌማን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች 19…
ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ሱልጣን በርሄ፣ ናትናኤል ሰለሞን እና ዳዊት ገብሩ አስቆጥረዋል፡፡
ድሬዳዋ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ዘርዓይ ገብረሥላሴ ከመረብ…
አዳማ ከተማ ባሕር ዳር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ባሕር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቢንያም አይተን እና ሙሴ ኪሮስ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
አዳማ ከተማ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ያሳካ ሲሆን÷በአንጻሩ ባሕር ዳር ከተማ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎችን…