ስፓርት
በኦሬገን ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ማራቶንና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ማራቶን እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ይጠበቃሉ።
ቀን 10 ሰዓት ከ15 ላይ የወንዶች ማራቶን የሚካሄድ ሲሆን፥ ሌሊሳ ደሲሳ፣ ሙስነት ገረመው፣ ሰይፉ ቱራ እና ዓየለ ቶላ ይሮጣሉ።
ምሽት 5 ሰዓት ላይም የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ይካሄዳል።
በዚህ ሩጫ በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ታደሰ ወርቁ ይሮጣሉ።
Read More...
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሊቱን በተካሄዱ የወንዶችና ሴቶች 1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች በሴቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች አልፈዋል፡፡
ጉዳፍ ጸጋይ 4፡01.28 ከምድብ አንድ 1ኛ፣ ፍረወይኒ ኃይሉ 4፡02.28 ከምድብ አንድ 4ኛ፣ ሂሩት መሸሻ 4፡04.05 በሆነ ጊዜ ከምድብ ሁለት 2ኛ በመሆን አልፈዋል፡፡…
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በለተሰንበት ግደይ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር በለተሰንበት ግደይ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በውድድሩ ኬንያውያን አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።
እጅጋየሁ ታየ ስድስተኛ እና ቦስና ሙላቴ ስምንተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።
በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ከተሳተፉት ሶስት አትሌቶች ሁለቱ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል
በአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሁለቱ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በመጀመሪያው ምድብ የወርቅውኃ ጌታቸው 2ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፍፃሜ ማለፍ ስትችል መቅደስ አበበ በሁለተኛው ምድብ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፍጻሜ ማለፏን…
በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጀመሪያ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በብቃት አልፈዋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገኑ 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ማጣሪያ ውድድሮች በወንዶች 3,000 ሜትር መሠናክል እና በሴቶች የ1,500 ሜትር ውድድሮች ስድስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በብቃት አልፈዋል።
3,000 ሜትር መሠናክል ወንዶች፣ ጌትነት ዋለ 8:17.49፣ ለሜቻ ግርማ 8:19.64 እና ኃ/ማርያም አማረ 8:18.34…
ዮርዳኖስ ዓባይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዮርዳኖስ ዓባይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን ክለቡ አስታወቀ፡፡
ድሬዳዋ ከተማ ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ÷ አሰልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይ ለአንድ ዓመት ክለቡን እንዲያሰለጥን ተሹሟል፡፡
ዮርዳኖስ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ወደ አሰልጣኝነቱ በመግባት በናሽናል…
18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀምራል
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሬጎን የሚካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል።
በውድድሩ ÷ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች በአጠቃላይ 40 ማለትም 21 ወንድና 19 ሴት አትሌቶችን እንደምታሳትፍ ተገልጿል።
አትሌቶቹ በ800 ሜትር፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር፣ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ በ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር እንዲሁም…